Daily Weather Report 25 December 12

Weather Summary for previous day

Dec. 11, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሻሁራ፣ ፓዌ፣ አሽ፣ ጂንካ እና ዲመካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኮረም፣ አለምከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ እና ሐሮማያ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the south, southwest, west, and northwestern parts of our country. In this regard, in Shahura, Pawe, Ashi, Jinka, and Dimeka received light to moderate amount of rainfall. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather was observed in the northeast, central, and eastern parts of our country. In this context, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Korem, Alemketema, Debreberhan, Bishoftu, Bui, Chelenko, Kulubi, and Haromaya.

Weather Forecast for next day

Dec. 13, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሜ፣ ጎፋ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጅ፣ ቦረናና ምስረቅ ቦረና ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ እና አፍዴር ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶቸች በመነሳት በጥቂት የምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ፣ ከፋ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ አዊ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን በአንዳንድ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow there will be Cloud coverage and accumulation across the southern and southeastern parts of the country which are in their second rainy season of the Bega. Accordingly, from southern Ethiopian region Wolaita, Gamo, Gofa, Kore, Gardula, Burji, Konso, Basketo, South Omo, and Gedeo zones; the Sidama region zones; from Oromia region Guji West Guji, Borena, and East Borena zones; and from Somali region Liben, Dawa, and Afder zones will receive light rain in a few places. Additionally, due to the intensifying weather systems, in Sheka, Bench Sheko, Dawro, west Omo, Konta, Kefa, Agnuak, Majang, Awi, south Gondar, north Wollo, and South Tigray zones will have light amount of unseasonal rainfall in a few places. On the other hand, the forecasts indicating the northern, northeastern, central, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather condition, and the daily minimum temperature in some highland areas will drop below 5°C.