Daily Weather Report 25 December 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በዳንግላ፣ ቻግኒ፣ መካነ ኢየሱስ፣ ደብረታቦር፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ቢላምቢሎ፣ ኦንጋ፣ አሺ፣ ጉበቲ፣ ቅዳሜገበያ፣ ኩሚ፣ ሳዉላ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the northwest, west, southwest and south parts of the country. In this regard, light to moderate rains were recorded in Dangila, Chagni, Mekane Yesus, Debretabor, Nekemte, Gore, Chira, Bilambilo, Onga, Ashi, Gubeti, Kidame Gebeya, Kumi, Sawula and Dilla. In contrast, dry, sunny and windy Bega weather condition was observed in the northeast, central and eastern parts of the country; accordingly, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few highlands of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጥቂት የአዊ ዞን፣ ደቡብና ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ የደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the next day, cloud coverage is expected over the southern, southwestern and western parts of our country. Associated with this, from Oromia region Borena, Guji and west Guji, Bale, west Arsi, Jimma and Ilubabor zones; from south Ethiopia region Walaita, Basketo, Gofa, Gamo, Kore, south Omo and Gedeo zones; Sidama region zones; from south west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Dawuro, Konta and west Omo zones and Majang zone of Gambella region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at some places. Moreover, due to the existing cloud coverage, a few areas of Awi zone, south and north Gondar, west and east Gojjam zones, southeast and east Tigray zones will experience light unseasonal rain. Conversely, the northeast, central, and eastern areas of the country will have dry, sunny, and windy Bega weather conditions, with the forecast information’s indicate that the daily minimum temperatures in the highlands of the country expected to drop below 5°C.