Daily Weather Report 25 December 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጥቂት የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቻግኒ፣ ሽንዲ፣ መካነ ኢየሱስ፣ ጎሬ፣ ካቺሴ እና ኩሚ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በደብረብርሀን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ፣ ኮረም እና በቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over a few parts of the northwest, west, southwest, and south of the country. In this respect, Chagni, Shindi, Mekane Yesus, Gore, Kachise, and Kumi received light rain. In contrast, dry, sunny, and windy Bega weather was observed in the northeast, central, and eastern parts of the country; in connection with this, the daily minimum temperature was recorded below 5°C in Debrebrehan, Bishoftu, Bui, Chelenko, Korem, and Kulubi.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወገልጤና፣ ኮረም፣ አምባማርያም፣ ባቲ፣ ጋሸና፣ ደብረብርሀን፣ አለምከተማ፣ ሾላገበያ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ማጃንግ፣ አኙዋክ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳዉሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, the northeast, central, southern highlands, and eastern parts of the country will have dry, sunny, and windy Bega weather condition. In this regard, the forecast indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in Wegeltena, Korem, Ambamariam, Bati, Gashena, Debrebrehan, Alemketema, Sholagebeya, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Haromaya, Chelenko, Kulubi, and Jigjiga. Conversely, there will be cloud coverage in the west, southwest, and south of the country; accordingly, Jimma, Ilubabor, west Arsi, Guji, Majang, Agnuak, Sheka, Kefa, Bench Sheko, Konta, Dawuro, west Omo, Walaita, Basketo, Gofa, Gamo, South Omo, and Gedeo zones and Sidama region zones will experience light to moderate rainfall at a few places.