Daily Weather Report 25 December 09

Weather Summary for previous day

Dec. 8, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በጋምቤላ እና በምዕራብ አማራ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሞያሌ፣ ሐዋሳ፣ ኩሉምሳ፣ አርጆ፣ ጊምቢ፣ ማሻ፣ ቅዳሜገበያ፣ ኩሚ፣ ሲቦ፣ ሽንዲ፣ ሻሁራ እና ቻግኒ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የነበራቸው ሲሆን፤ በአንዳንድ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ በታች እና በጨለንቆ ደግሞ -2 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed in southern and western Oromia, Sidama, southern and southwestern Ethiopia, Gambella, and the western Amhara region. In this regard, light to moderate rains were recorded in Moyale, Hawassa, Kulumsa, Arjo, Gimbi, Masha, Kidame Gebeya, Kumi, Sibo, Shindi, Shahura, and Chagni. Conversely, the northeastern, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather; the daily minimum temperature was recorded as below 5 degrees Celsius in some highlands of the country and -2 degrees Celsius in Chelenko.

Weather Forecast for next day

Dec. 10, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን በአንዳንድ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud coverage over the southern, southwestern, and western parts of our country. Associated with this, from the south Ethiopian region Walaita, Basketo and Gedeo zones; Sidama region zones; from Oromia region Guji, west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele and east Wellega zones; from the south west Ethiopian region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Dawuro, Konta and west Omo zones, and from Gambella region Agnuak, Itang and Majang zones will have light to moderate (1-29 mm) rainfall at a few places. On the other hand, the northeastern, central, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather, with the minimum temperature of the day below 5°C in some highlands.