Daily Weather Report 25 December 08

Weather Summary for previous day

Dec. 7, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወላይታ ሶዶ፣ ሐዋሳ፣ አንጋጫ፣ አማን፣ ቴፒ፣ ቢላምቢሎ፣ ሙጊ እና ትንሹ ሜጢ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጋሸና፣ ኮረም፣ ዳባት፣ አለምከተማ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ እና ቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the southern, southwestern and western parts of the country had cloud coverage. In this respect, Walaita Sodo, Hawassa, Angacha, Aman, Tepi, Bilambilo, Mugi and Tinishu Meti received light rain. On the other hand, the northeastern, central and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy Bega weather; accordingly the minimum temperature of the day recorded below 5 degrees Celsius in Gashena, Korem, Dabat, Alemketama, Bishoftu, Bui, Chelenko and Kulubi.

Weather Forecast for next day

Dec. 9, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ ኦሮሚያ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳዉሮ፣ ወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ጌዲኦ፣ ኮሬ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the northeast, central and eastern parts of our country will experience dry, sunny and windy Bega weather. In this regard, numerical weather forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in the eastern Amhara, central, southern highlands and eastern Oromia. Conversely, the western, southwestern and southern portions of the country will have cloud coverage, associated with this, the zones of Kelam Wellega, Ilubabor, Jimma, west Arsi, Guji and west Guji, Itang, Agnuwak, Majang, Sheka, Kefa, Bench Sheko, Konta, Dawuro, Walaita, Basketo, Gofa, Gamo, Gedeo, Kore and Sidama region zones will have light rain in a few places.