Daily Weather Report 25 December 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሳዉላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ቴፒ፣ ማሻ፣ ፉኝዶ፣ ጭራ እና ነፋስመዉጫ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለባቸው ሲሆን፣ በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the southern, southwestern, western, and northwestern parts of the country experienced occasional cloud coverage. Associated with this, Sawula, Walaita, Sodo, Tepi, Masha, Fugnido, Chira, and Nefasmewucha received light to moderate rainfall. In contrast, the northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather; accordingly, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few areas of the east Amhara region and the highland areas of the eastern portions of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአንዳንድ የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቀለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ወላይታ እና ጌድኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጥቂት የአዊ ዞን፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች አነስተኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the upcoming day, there will be cloud coverage over some parts of the west, southwest, and south of the country. In connection with this, the zones of Kelam and west Wellega, Ilubabor, Buno Bedele, Jimma, west Arsi, Guji and west Guji; zones of Asossa and Mao Komo; zones of Itang, Agnuak and Majang; zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro; zones of Hadiya, Kembata and Tembaro; Basketo, Gofa, Gamo, Walaita and Gedeo zones and Sidama region zones will receive light rain at a few places. Furthermore, due to the existing cloud coverage, a few areas of Awi zone, south Gondar, west, and east Gojjam zones will experience light unseasonal rain. On the other hand, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will be observed over the northeastern, central, and eastern parts of our country, with forecast information indicating that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius.