Daily Weather Report 25 December 06

Weather Summary for previous day

Dec. 5, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች፣ ደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በባሌሮቤ፣ አደሌ፣ ጃራ፣ ዲላ፣ ጂንካ፣ አማን እና ቴፒ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the south highlands, southern and western Oromia, Gambella, south and south west Ethiopia. In this regard, Balerobe, Adele, Jara, Dilla, Jinka, Aman, and Tepi received light to moderate rainfall. On the other hand, the northeastern, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather; in this respect, in a few highlands of the country, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Dec. 7, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል በጥቂት የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቀለም ወለጋ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጥቂት የደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች አነስተኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልባቸው ሲሆን፤ በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the next day, there will be cloud coverage over the southern, western, and southwestern parts of the country. In this regard, in a few areas of Guji and west Guji, Bale, west Arsi, Jimma, Ilubabor, Kelam Wellega, and Buno Bedele zones of Oromia region; Basketo, Gofa, Gamo, and Gedeo zones of south Ethiopia region; zones of Sidama region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, and Konta zones of south west Ethiopia region; Agnuak and Majang zones of Gambella region will receive light rain at their few places. In addition, due to the cloud coverage, there will be light unseasonal rain over a few areas of the south Gondar, west, and east Gojjam zones. Conversely, the Bega dry, sunny and windy weather will be observed in the northeastern, central and eastern parts of the country; accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5 degrees Celsius in a few places.