Daily Weather Report 25 December 05

Weather Summary for previous day

Dec. 4, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በጋምቤላ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአባጃራ እና ሲቦ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኮረም፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲ ሮቤ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ እና ሐሮማያ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover southern and southwestern Ethiopia, as well as western Oromia and Gambella. In association with this, light rainfall was received in Abajara and Sibo. The dry, sunny, and windy Bega weather conditions were observed over the northeastern, central, southern highland and eastern parts parts of the country. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5°C in Korem, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Chelenko, Kulubi, and Haromaya.

Weather Forecast for next day

Dec. 6, 2025

በነገው ዕለት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች እንዲሁም ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት የባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ማጃንግ ዞን እንዲሁም የሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern parts of the country. Accordingly, in a few Wolaita, Gofa, Basketo, and Gedeo zones in southern Ethiopia, the zones of the Sidama region, Guji zone and western Guji, will receive light rain in areas. Additionally, due to the cloud cover, Bale, west Arsi, Jimma, and Ilubabor zones; Sheka, Bench Sheko, Dawro, and west Omo zones, as Majang zone; Hadiya, Kembata, and Tembaro zones, will have light unseasonal rainfall in a few places. On the other hand, forecasts indicating that in the northeast, east, and central parts of the country will experience Bega season dry, sunny and windy weather conditions with the daily minimum temperature is expected to drop below 5°C.