Daily Weather Report 25 December 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአምባማሪያም፣ መሀልሜዳ፣ ቡኢ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ፣ ኮረም እና ጋሸና የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, the northeast, central, southern highlands, and eastern parts of our country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this respect, the minimum temperature of the day was recorded below 5°C in Ambamariam, Mehalmeda, Bui, Arsirobe, Balerobe, Chelenko, Kulubi, Haromaya, Korem, and Gashena. In contrast, the southern, southwestern, and western parts of the country had occasional cloud coverage.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ ኦሮሚያ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም የጅማ፣ ቀለም፣ ኢሉባቦር፣ ባሌ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ አኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ጌድኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the next day, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will prevail over the north, northeastern, central, and eastern parts of the country. Accordingly, the weather forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in some areas of east Amhara, central, south, and east Oromia region, with the night and morning cold will continue. Conversely, there will be cloud coverage over the west, southwest, and south of portions of our country. In this regard, the zones of Jimma, Kelam, Ilubabor, Bale, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Agnuwak, Majang, Gofa, Gamo, Gedeo, and Sidama region will have light rain in their few places.