Daily Weather Report 25 December 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወገልጤና፣ በአምባማሪያም፣ አለምከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ጋሸና፣ ቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ፣ ጨፌዶንሳ፣ ጅግጅጋ እና ጅማ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የምዕራብ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, the northeast, central, southern highlands, and eastern parts of our country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5°C in Wegeltena, Ambamariam, Alemketema, Debrebrehan, Gashena, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Balerobe, Chelenko, Kulubi, Haromaya, Chaffedonsa, Jigjiga, and Jimma. In contrast, cloud coverage was observed over a few areas of the west, south, and southwest of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአምባማሪያም፣ ወገልጤና፣ ባቲ፣ ጋሸና፣ አለምከተማ፣ ሾላገበያ፣ ደብረብርሀን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆንና፤ የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የሸካ፣ ከፋ፣ ማጃንግ፣ ኢሉባቦር እና ጅማ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will be observed in the northeastern, central, southern highlands, and eastern parts of our country. Accordingly, the numerical weather forecast indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in Ambamariam, Wegeltena, Bati, Gashena, Alemketema, Sholagebeya, Debrebrehan, Bishoftu, Bui, Emdibir, Arsirobe, Balerobe, Haromaya, Chelenko, Kulubi, and Jigjiga; and the night and morning cold will continue the same conditions. Conversely, there will be cloud coverage over the west, southwest, and south of the country, while Sheka, Kefa, Majang, Ilubabor, and Jimma zones will have light rain at a few places.