Daily Weather Report 25 December 02

Weather Summary for previous day

Dec. 1, 2025

በትናንትናዉ ዕለት ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ ጋሸና፣ ባቲ፣ በአምባ ማርያም፣ በወገልጤና፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ እምድብር፣ አርሲ ሮቤ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ፣ ጅግጅጋ እና ጨፌዶንሳ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በምዕራብ እና በደቡብምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ሳሳ ያለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday, dry, sunny, and windy Bega weather conditions were observed over much of the northeastern, central, southern highlands, and eastern parts of the country. In this regard, in Debark, Gashena, Bati, Amba Maryam, Wegeltena, Bishoftu, Bui, Emdibir, Arsi Robe, Bale Robe, Chelenko, Kulubi, Haromaya, Jigjiga, and Chefedonsa reported daily minimum temperatures dropping below 5°C.

Weather Forecast for next day

Dec. 3, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወገልጤና፣ ባቲ፣ አምባማርያም፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ ደብረብርሀን፣ እንዋሪ፣ አለምከተማ፣ ሾላገበያ፣ ደባርቅ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲ ሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ጅግጅጋ እና እምድብር የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን እና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ምዕራብና ደቡብምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቤንችሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, much of the northeastern, eastern, southern highlands and central parts of the country will experience Bega season dry, sunny, and windy weather conditions. In association with this, in Wegeltena, Bati, Amba Maryam, Were Ilu, Mehal Meda, Debre Berhan, Enwari, Alem Ketema, Shola Gebeya, Debark, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya, Chelenko, Kulubi, Jigjiga, and Emdibir the daily minimum temperature is expected to drop below 5°C; and Cold conditions are likely to persist during the night and early morning. On the other hand, there will be occasional cloud cover the south, west, and southwestern parts of the country. Accordingly, in a few places of Ilubabor, Jimma, Bench Sheko, Sheka, Kefa, and Majang zones will receive light rain.