Daily Weather Report 25 December 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በጋምቤላ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያዞ በሼንዲ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ በደብረብርሀን፣ በጨለንቆ፣ በቁልቢ፣ በቢሾፍቱ፣ በሐሮማያ፣ በባሌ ሮቤ፣ በእምድብር፣ በጋሸና፣ በቡኢ እና በአርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the skies were cloudy over southern and southwestern Ethiopia, in western Oromia and Gambela. Light rain was recorded in some places of Shendi. Meanwhile, northern and eastern, central and eastern parts of the country experienced the dry, sunny and windy conditions typical of the season. In Wegeltena, Debre Berhan, Chelenko, Kulbi, Bishoftu, Haromaya, Bale Robe, Emdibir, Gashena, Bui and Arsi Robe the daytime maximum temperatures were recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እንዲሁም የጅማና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆንና፤ የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜም እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, during the day there will be cloud cover and light rain in some southern and south-eastern areas as well as in parts of the west and south-west of the country. In association with this, light rain is expected in a few places of Gedeo Zone in the Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region; in zones of Sidama and Jimma and Iluababora; in Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia; and in the Agnuwak and Majang zones of Gambela Region. Elsewhere, in the north-east, east, southeastern highlands and central parts of the country, the Bega conditions will be dry, sunny and windy. Daytime maximum temperatures are forecast to below 5 degrees Celsius, and early-morning and nighttime cold is also expected, according to the forecast.