Daily Weather Report 25 August 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጃራ እና አዴት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there were heavy clouds, fog, and mist over many parts of our country where the winter rain was beneficial. Along with this, light to moderate rainfall (ranging from 1 to 29 mm) was recorded in many areas. Additionally, in Jara and Adet, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ሀሪ እና ማሂ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሊሙ፣ ካማሺ፣ ሻርቆሌ፣ሆሞሻ፣አቤ ዶንጎሮ፣ ናጆ፣ ሳሲጋ፣ጊምቢ፣ ጫዋቃ፣አይራ፣ዳሌ ዋባራ፣ዲጋ፣ጉሊሶ፣ጉቶ ጊዳ፣ሀሮ፣ባኮ ቲቤ፣ጂማ አርጆ፣ባዳሌ ዙሪያ፣ኢሉ ጋላነ፣ጊዳ ኣያና፣ዳኖ፣ጂባተ፣ሌቃ ዱላቻ፣ማና ሲቡ፣ጋጂ እና ሆማ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, areas of our country that benefit from winter rains will experience heavy cloud cover, fog, and mist. Additionally, the following zones are expected to receive light to moderate rainfall in many places:From the Tigray region: Central, Northwest, Southeast, South, and East zones;From the Amhara region: North, West, South, and Central Gondar; West and East Gojjam; Awi; North and South Wollo; the special Oromia zone; North Shewa and Wag Hemra zones;From the Oromia region: Jimma, Illubabor, Buno Bedelle; West, East, Kelem, and Horogudru Welega; West, Southwest, East, and North Shewa; Arsi and West Arsi; West and East Hararghe; Borena; Bale and East Bale; Guji and West Guji zones;Addis Ababa; Dire Dawa; Harar;From Gambela region: Itang, Nuer, Agnuak, and Majang zones;From Benishangul Gumuz region: Asosa, Mao Komo, Kamashi, and Metekel zones;From Southwest Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo, and Dawuro zones;From Central Ethiopia region: Gurage, East Gurage, Kebena special zone, Mareko special zone, special zones of M, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tambaro zones;From Sidama region zones;From Southern Ethiopia region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burji, Konso, South Omo, and Gedeo zones;From Afar region: Gabi, Hari, and Mahi zones;From Somali region: Sitti and Fafan zones.Furthermore, due to prevailing weather disturbances, the following areas are forecast to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours: Limu, Kamashi, Sharkole, Homosha, Abe Dongoro, Najo, Sasiga, Gimbi, Chewaka, Ayira, Dale Wabera, Diga, Guliso, Guto Gida, Haro, Bako Tibe, Jimma Arjo, Badale surroundings, Ilu Galan, Gida Ayana, Dano, Jibat, Leka Dulacha, Mana Sibu, Gaji, and Homa.