Daily Weather Report 25 August 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሀሮ፣ ዳንግላ፣ ኢጃጂ እና ሆሳእና በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday The areas of our country that benefit from the Kiremt rains had cloud cover. In connection with this, many of them received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Haro, Dangla, Ijaji and Hossain in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጅ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሁለትእጅነሴ፣ አዎበል፣ አንጎለላጠራ፣ ምንጃር ሸንኮራ፣ አለልቱ፣ አምቦ ዙርያ፣ ኢሉ፣ ሰበታ ሀዋስ፣ አመያ፣ ወሊሶ፣ ሊበን፣ ዱግዳ፣ መርቲ፣ ሰዴ፣ ሙኒሳ፣ ጊምቢ፣ ሳዮ፣ አንፊሎ፣ ቡሬ፣ መቱ፣ መና፣ ኦሞናዳ፣ ጫጫ፣ ሶዶ፣ ሊሞ፣ ማሻ፣ ጨና፣ ጋምቤላ፣ አቃቂ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow There will be strong cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from Kiremt rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, East, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Itang, Nuer, Agnua and Majang zones from Gambella region; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage from Central Ethiopia region, East Gurage, Marekko Special Zone, Mem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; Sidama Region zones; Wolaita, Gamo, Gofa, Gardula, Burj and Gedio zones from the Southern Ethiopia Region; Yeklabeti, Gabi, Hari and Fanti zones from the Afar Region andAnd the Siti and Fafen zones of the Somali region will receive light to moderate rainfall at many places. In addition, based on the strengthening weather events, the areas of Bilal-e-Nesse, Awobel, Angol-Lazara, Menjar Shenkora, Alleltu, Ambo Zuria, Ilu, Sebeta Hawas, Amaya, Wolisso, Liben, Dugda, Merti, Sedeh, Munisa, Gimbi, Sayo, Anfilo, Bure, Methu, Mena, Omonada, Chacha, Sodo, Limo, Masha, Chena, Gambella, Akaki and Addis Ababa will experience heavy rainfall of more than 30mm within 24 hours.