Daily Weather Report 25 August 28

Weather Summary for previous day

Aug. 27, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ14 በሚያህሉ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In connection with this, many areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, 14 areas recorded heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 29, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ እንደሚስፋፉ እና እንደሚጠናከሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በአድዋ፣ የጭላ፣ ሽሬእንዳስላሴ፣ ታህታይ ማይጨው፣ አቢአዲ፣አሳይታ፣ ያንጉዲ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ባቢሌ፣ግራዋ፣ አላማጣ፣ ሰቆጣ፣ አምደወርቅ፣ ጋሸና፣ ወገልጤና፣ ደምበጫ፣ ወንበራ፣ ደብረብርሃን፣ ሾላ ገበያ፣ በደሌ፣ ያዮ፣ ጅማ፣ ሰተማ፣ ሸካ፣ ወንጪ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Our numerical forecast indicates that weather conditions conducive to the formation of kiremet rains will further expand and intensify. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Nuer, Agnua and Majang zones from Gambella region; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, M's Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; Sidama Region zones, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones from the Southern Ethiopia Region; Hausi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti zones from the Afar Region and The Siti and Fafen zones of the Somali region will experience light to moderate rainfall at many places. In addition, due to the strengthening weather events, Adwa, Yecla, Shireendasalasse, Tahtai Maichew, Abiadi, Asaita, Yangudi, Gewane, Awash Arba, Babile, Grawa, Alamata, Sekota, Amdework, Gashena, Wogeltiye, Dembecha, Wenbera, Debre Berhan, Shola Gebeya, Bedele, Yayo, Jimma, Setema, Sheka, Wonchi and Addis Ababa will experience heavy rainfall of more than 30mm within 24 hours.