Daily Weather Report 25 August 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሸርኮሌ፣ አልጌ፣ ሮቢት፣ ጎብዬ እና ወሊሶ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremt rains. In connection with this, many areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Sherkole, Alge, Robit, Gobye and Wolisso within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በአድዋ፣ ቆላተምቤን፣ ሐውዜን፣ አዲግራት፣ ሰቆጣ፣ ኮረም፣ ቡግና፣ ላሊበላ፣ መቄት፣ እንሳሮ፣ ፍቼ፣ ደብረሲና፣ አንጎለላ ጠራ፣ አሳይታ፣ ያንጉዲ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ባቢሌ እና ግራዋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow There will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Nuer, Agnuak and Majang zones from Gambella region; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; From the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; from the Sidama Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio Zones; from the Afar Region, Hausi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti Zonesand Fanti zones and the Siti and Fafne zones of the Somali region will experience light to moderate rainfall at many places. In addition, due to the strengthening weather events, Adwa, Qolatembe, Hawzen, Adigrat, Sekota, Korum, Bugna, Lalibela, Meket, Ensaro, Fiche, Debresina, Angolala Chara, Asita, Yangudi, Gewane, Awash Arba, Babile and Grawa will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours.