Daily Weather Report 25 August 26

Weather Summary for previous day

Aug. 25, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነፋስ መውጫ፣ ድሬዳዋ፣ ነገሌ፣ ሆሳዕና፣ ያንፋ እና አዲስ ዘመን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the areas of our country that benefited from the kiremet rains had cloud cover and received light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Nifas Mewicha, Dire Dawa, Negele, Hosaena, Yanfa and Addis Zemen in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 27, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዳንሻ፣ ማይጨው፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ሰቆጣ፣ አምደወርቅ፣ ጋሸና፣ ወገልጤና፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ ዱለቻ፣ አሚባራ፣ አይሻ፣ ሽንሌ፣ ኤረር፣ እምድብር፣ አለታወንዶ፣ አባያ፣ ጎባ እና ጎሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of kiremet rains will strengthen. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Agnuak and Majang zones from Gambella region; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; The Central Ethiopian Region includes Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; the Sidama Region zones; the Southern Ethiopian Region includes Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones; the Afar Region includes Housi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti zones; and the Somali Region includes Sitti and Fafen zones Light to moderate rainfall is expected in many areas. In addition, based on the intensifying weather events, Dansha, Maychew, Korem, Alamata, Sekota, Amdework, Gashena, Wogeltiya, Awash Fentale, Dulecha, Amibara, Aisha, Shinle, Erer, Emdbir, Aletwendo, Abaya, Goba and Goro will experience heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours.