Daily Weather Report 25 August 25

Weather Summary for previous day

Aug. 24, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአቦቦ፣ ሐሮ፣ መንዲዳ እና መንደር 11 በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In connection with this, many places received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Abobo, Haro, Mendida and Village 11 in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 26, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በማይካድራ፣ ዳንሻ፣ ሽራሮ፣ ምዕራብ አርማጮ፣ ሰመራ፣ ሚሌ፣ ሽንሌ እና አይሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale, Guji and West Guji zones; ; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Benishangul Gumuz Region: Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel Zones; Southwestern Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; Central Ethiopia Region: Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; Sidama Region zones, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopia Region; Hausi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar Region and Siti and Fafen zones of the Somali Region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, based on the intensifying weather events, Maikadra, Dansha, Shiraro, West Armacho, Semera, Mile, Shinle, and Aisha will experience heavy rainfall within 24 hours.