Daily Weather Report 25 August 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በደቡብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል። በተጨማሪም በሲሪንቃ፣ ዳንግላ፣ ጅማ እና አርሲሮቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the country that benefited from the Kiremt rainfall experienced cloudy weather conditions. In line with this, many areas received light to moderate rain (1-29 mm). Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Sirinka, Dangila, Jimma, and Arsi Robe over the past 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ፣ ጋቢ እና አዉሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በባቲ፣ ወረባቦ፣ ቃሉ፣ አርጎባ፣ ሀርቡ፣ መቅደላ፣ ሳይንት እና መካነሰላም በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud cover and accumulation over the country that benefits from the Kiremt rainfall. In this regard, the western, central, northwestern, southeastern, southern, and eastern zones of Tigray region; the western, northern, southern, and central Gondar, northern, western, and east Gojam, Awi zone, northern and southern Wollo, Oromo Special Zone, North Shewa and Waghemra zones of Amhara region; the Kilbeti, Fanti, Hari, Gabi and Awsi zones of Afar region; the Metekal, Asosa, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West, Southwest and East Shewa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararge zones of Oromia region, Addis Ababa; Dire Dawa; Majang and Agnuak zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawuro and Konta zones of the South west Ethiopia region; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Ale, Konso, Gardula, South Omo and Gedeo zones of the South Ethiopian region; Sidama region zones and the Siti Zone of the Somali region will received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, Bati, Werebabo, Kallu, Argoba, Harbu, Mekdella, Saint, and Mekaneselam will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.