Daily Weather Report 25 August 21

Weather Summary for previous day

Aug. 20, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል። በተጨማሪም በስንቃጣ፣ አድዋ፣ አጽቢ፣ ሽሬእንደሥላሴ፣ ውቅሮ፣ ፅጌሬዳ፣ የጭላ፣ ማይሀንሳ፣ ወርቅአምባ፣ አዲስ ዘመን፣ ደብረታቦር፣ መካነሰላም፣ አርጆ፣ ሀሮ እና የሪ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30-68.9 ሚ.ሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the western half, northeast, central, east, and southern areas of our country. In line with this, many locations received light to moderate amounts of rain (1-29 mm). Additionally, heavy rainfall amounts between 30-68.9 mm were recorded in Senkata, Adwa, Atsibi, ShreEndesilase, Wukro, Tsigereda, Yechila, Mayhansa, Work Amba, Addis Zemen, Debretabor, Mekaneselam, Arjo, Haro, and Yeri, within a 24-hour.

Weather Forecast for next day

Aug. 22, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ቀጣይነት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ፤ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በባቲ፣ ቃሉ፣ ጭፍራ፣ ካማሽ፣ ዛይ፣ ዴምበ፣ ሃሮሊሙ፣ ጊዳአያና፣ ቦቶርጦላይ፣ ኖኖ፣ ኦሞናዳ፣ ማንቾ፣ ዴቦ፣ አመያ፣ ወንጭ፣ ወሊሶ፣ ሙኒሳ፣ የም፣ ቸሃ፣ እነሞር፣ አሜካ፣ ጊቤ፣ ጎምቦሮ፣ ምዕራበ ሶሮ፣ ዳኖ፣ ጠምባሮ፣ ቦሎሶ ቦምቤ፣ ኪኖዶኮይሻ፣ ዛባጋዞ፣ ሎማ፣ ዲሳ፣ ማሪማነሳ፣ ኮንታኮይሻ፣ ቻታ፣ ማጂ እና መንቲሻሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።

Tomorrow, the forecast information shows that weather conditions favorable to the formation of Kiremt rainfall will continue. In association with this, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; from Afar region Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones, from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, Gardula, Alle, Burji, Konso and Basketo zones and from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in most areas. Additionally, Due to the occasional intensifying weather events, in Bati, Kalu, Tembaro, Zayi, Dembe, Harolimu, Gidaayana, Botortolai, Nono, Omonada, Mancho, Debo, Amaya, Sling, Woliso, Munissa, Yem, Cheha, Enemor, Ameka, Gibe, Gomboro, Mirab Soro, Dano, Tembaro, Boloso Bombe, Kinodokoisha, Zabagazo, Loma, Disa, Marimana, Kontakoysha, Chata, Maji, and Mentishasha are expected to experience heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour period.