Daily Weather Report 25 August 18

Weather Summary for previous day

Aug. 17, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በደቡብ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ እና የተጠናከረ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል። በተጨማሪም አስራ አንድ በሚያህሉ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, widespread and intense cloud coverage was observed over the Kiremt beneficial rainfall area, as well as in the southern region. In connection with this, many areas received light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 millimeters. Furthermore, in about eleven locations, heavy rainfall exceeding 30 millimeters was reported within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 19, 2025

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት የሚኖራቸው ሲሆን ወደ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎችም እንደሚስፈፉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ፣ ጋቢ እና አዉሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤሬር፣ ኖጎብ፣ ሸበሌ እና ቆራሄ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፂምቢላ፣ አሕፈሮም፣ ንአደር፣ እግላ፣ አድዋ፣ እንዳባ ፃህማ፣ ደጓተምቤን፣ ቢዜት፣ ጋንታ አፈሹም፣ ሀውዜን፣ አፅቢ፣ ሳሓርቲ፣ አባርጋለ፣ ደባርቅ፣ በይዳ፣ ሳሒላ፣ አንጎት፣ ጊሽራቤል፣ አንጾኪያ፣ አይሻ፣ ጋብላሉ፣ ጊዳሚ፣ አንፊሎ፣ ጨዋቃ፣ ጅማ አርጆ፣ ቀርሳ (ጅማ)፣ ኦሞ ናዳ፣ አዳማ ቱሉ፣ ጠና፣ ጥዮ፣ ሮቤ፣ ጎሎልቻ፣ አርሲ ነገሌ፣ ነነሴቦ፣ አዳባ፣ ባሌ፣ ዲንሾ፣ የም ልዩ ዞን፣ ጊቤ፣ ጎምቦራ፣ ዉልበርግ፣ ዳሎቻ፣ ጠምባሮ፣ ቦሎሶሶሬ፣ ዳሞትሶሬ፣ ክንዶኮይሻ፣ ሁምቦ፣ ሶዶዙሪያ፣ ኮንታ ኮይሻ፣ መኒት ሻሻ፣ አሌ፣ ማሊኤ፣ በናፀማይ፣ ቢላቴ፣ ሐዋሳ ዙሪያ፣ ደራራ እና መንገሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

For the next day, the forecast information indicates rain-producing weather phenomena will continue over areas of the country that benefit from the Kiremt rain, and also spread to the south and southeast parts of the country. In this respect, the west, central, north west, south east, south and east zones of Tigray region; the west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo nation special zone, north Shewa and Waghemra zones of Amhara region; Kilbeti, Fanti, Hari, Gabi and Awusi zones of Afar region; Metekal, Kamashi, Asossa and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horro Guduru, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, west and east Hararge zones o Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Majang, Nuwer, Itang and Agnuak zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones of south west Ethiopia region; Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones of the central Ethiopia region; Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, Ale, south Omo and Gedeo zones of the south Ethiopia region; Sidama region zones and Siti, Fafen, Jarar, Erer, Nogob, Shebelle and Korahe zones of the Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, in Tsimbila, Ahferom, Neader, Egla, Adwa, Endaba Tahma, Degua Temben, Bizet, Ganta Afeshum, Hawzen, Atsebi, Saharti, Abargale, Debarq, Beyda, Sahila, Angot, Gishirabel, Antsokia, Aisha, Gabilalu, Gidami, Anfilo, Chewaka, Jimma Arjo, Kersa (Jima), Omo Nada, Adama Tulu, Tena, Tiyo, Roobee, Gololcha, Arsi Negelle, Nenesebo, Adaba, Bale, Dinshoo, Yem special zone, Gibe, Gombora, Wulbarg, Dalocha, Tembaro, Bolososore, Damotsore, Kindokoisha, Humbo, Sodozuria, Kontakoisha, Menit Shasha, Ale, Malie, Benatsmay, Bilate, Hawassa Zuria, Derara and Mengesh will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.