Daily Weather Report 25 August 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያየዘም በደባርቅ፣ ጎንደር፣ ሻሁራ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ የትኖራ፣ ነፋስመውጫ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ ወረኢሉ፣ አለምከተማ፣ ሾላገበያ፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ፣ ጊምቢ፣ ጨዋቃ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ሻምቡ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ኢጃጅ፣ ካችሴ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ፣ መተሀራ፣ አቦምሳ፣ ቁልምሳ፣ ባቱ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ጃራ፣ ቦሬ፣ ላንጌ፣ መልካጀብዱ፣ ኩርፋጨሌ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጎብየሬ፣ ጋምቤላ፣ ሙጊ፣ ኦቦመርጋ፣ ሲቦ፣ ይና፣ ማጅ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታሶዶ፣ ብላቴ፣ ዲላ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ቡርጅ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል። በተጨማሪም በባህርዳር፣ መሀልሜዳ፣ እንዋሪ፣ ነቀምቴ፣ ጋቲራ፣ አዳማ፣ ኑራኤራ፣ ገለምሶ፣ ሜኢሶ፣ ጨለንቆ፣ ቁሉቢ፣ ሐሮማያ፣ ሂርና እና ደንገጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was strong cloud cover over Kiremt rain benefiting areas of our country. In this regards, in Debark, Gondar, Shahura, Dangla, Motta, Yetnora, Nefasmewicha, Wegeltena, Combolcha, Cheffa, Bati, Wereilu, Alemketama, Sholagebeya, Chifra, Semera, Gewane, Awasharba, Gimbi, Chewaka, Arjo, Bedele, Shambu, Chira, Jimma, Sokoru, Ejaji, Kachise, Ambo, Woliso, Addis Ababa, Bishoftu, Metehara, Abomsa, Kulumsa, Batu, Arsi Robe, Bale Robe, Jara, Bore, Lange, Melekjbidu, Kurfachele, Harar, Dire Dawa, Gobiyere, Gambella, Mugi, Obomerga, Sibo, Yina, Maji, Emdibir, Hosanna, Werabe, Hawassa, Wolaitasodo, Bilate, Dilla, West Abaya, Jinka, Konso and Burj received light to moderate amount of rainfall. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour was recorded in Bahir Dar, Mehalmeda, Enewari, Nekemte, Gatira, Adama, Nuraera, Gemelso, Meiso, Chelenko, Kulubi, Haramaya, Hirna, and Dengego.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች እንዲሁም በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ፤ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በጸለምት፣ አስገዲ፣ ጽምብላ፣ እገላ፣ ጋዘጊብላ፣ ላስታ፣ አንጎት፣ ዋድላ፣ ሃብሩ፣ ወረባቦ፣ ባቲ፣ እዋ፣ ቢዱ፣ ኤሊዳር፣ ደዌ፣ ሐረር፣ ጉርሱም፣ ሀሮማያ፣ ፍዲስ፣ ግራዋ፣ መልካባሎ፣ ደደር፣ ቀርሳ (ምስራቅ ሀረርጌ)፣ በደኖ፣ ገመችስ፣ መሰላ፣ ቱሎ፣ ሀባሮ፣ ቦቃ፣ አሴኮ፣ መርቲ፣ አርሲ ነገሌ፣ ሻላ፣ ሻሸመኔ፣ ኮፈሌ፣ ቆቆሳ፣ ነንሴቦ፣ ጎባ፣ ሀረናቡልቅ፣ ሀዋሳ ዙሪያ፣ ብላቴ፣ ወንዶገነት፣ ማልጋ፣ ኦዶሻኪሶ፣ ዳሰነች፣ ሀመር፣ ቱሊጉላር፣ ሻዕቢያ እና ጎልጃኖ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። ስለሆነም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አከባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡
Tomorrow, Weather conditions conducive to the formation of rain will continue over the Kiremt rain-benefiting areas, as well as the southern and southeastern parts of our country. In association with this, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Boren and east Borena zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; from Afar region Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones, from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, Gardula, Alle, Burji, Konso and Basketo zones and from Somali region Siti, Fafen, Jarar, Nogob, Erer, Afder, Shebelle, Korahe and Doolo and zones will receive light to moderate rainfall in most areas. Additionally, due to the intensifying weather events, in Tselemt, Asgedi, Tsimbla, Egela, Gazegibla, Lasta, Angot, Wadla, Habru, Werebabo, Bati, Ewa, Bidu, Elidar, Dewe, Harar, Gursum, Haramaya, Fedis, Girawa, Melk Baloo, Deder, Keresa (East Hararge), Dano, Gamache's, Mesala, Tulo, Habaro, Boka, Aseko, Merti, Arsi Negele, Shala, Shashemene, Kofele, Kokosa, Nensebo, Goba, Harenabuluk, Hawassa Zuriya, Bilate, Wondogenet, Malga, Odoshakiso, Dasench, Hamer, Tuliguled, Shabeely, and Goljano will experience heavy rainfall within a 24-hour that may result in flash flooding. Consequently, the Ethiopian Meteorological Institute advises the community and relevant Stakeholders to implement necessary precautions in the flood prone areas.