Daily Weather Report 25 August 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም መቀሌ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ አዴት፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ደብረታቦር፣ ነፋስመውጫ፣ አምባማርያም፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ እንዋሪ፣ ሾላገበያ፣ ሻምቡ፣ ካችሴ፣ ደምቢዶሎ፣ ጎሬ፣ ቁልምሳ፣ አደሌ፣ ባሌሮቤ፣ ቁሉቢ፣ ሂርና፣ ካራሚሌ፣ ደንገጎ፣ ሆሳዕና፣ ጋምቤላ፣ አሽ፣ ባሮቦንጋ፣ ኩሚ፣ ተርጫ እና ብላቴ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል።
Yesterday, there was cloud cover over the northwest, central, northeast, east, southwest, and southern parts of our country. In this regard, Mekelle, Debark, Gondar, Aykel, Bahir Dar, Dangla, Chagni, Adet, Debrework, Debre Markos, Yetnora, Debretabor, Nefasmewicha, Amba Mariam, Combolcha, Cheffa, Wereilu, Mehalmeda, Enwari, Sholagebeya, Shambu, Kachise, Dembidolo, Gore, Kulumsa, Adele, Bale Robe, Kulubi, Hirna, Karamile, Dengego, Hosanna, Gambella, Ashi, Barobonga, Kumi, Tercha, and Bilatte received light to moderate (1-29 mm) amounts of rain.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች እንዲሁም በደቡብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የተስፋፋ እና የተጠናከረ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ፤ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በፀሀይ ሀይል ታግዘው ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በአንጎት፣ ዋድላ፣ ዳውንት፣ ደላንታ፣ መቅደላ፣ ወግዲ፣ ከለላ፣ ጃማ፣ መንዝቀያ፣ ሞረትና ጂሩ፣ እንሳሮ፣ ቢዱ፣ ኮሪ፣ ዱብቲ፣ ኤሊዳር፣ ማባይ፣ ጊምቢቹ፣ አዳአ፣ ቢሾፍቱ፣ አቃቂ፣ አዳማ፣ ሎሜ፣ ሊበንችቋላ፣ ዶዶታ፣ ዝዋይ ዱግዳ፣ ሂቶሳ፣ አጋርፋ፣ ኦሞበየማ፣ የም፣ ጊቤ፣ ማጅ እና ሳላማጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።
Tomorrow, there will be intensified and widespread cloud cover over the Kiremt rain-benefiting areas and the southern parts of our country. In association with this, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Boren and east Borena zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; from Afar region Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones, from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, Gardula, Alle, Burji, Konso and Basketo zones and from Somali region Silte and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in most areas. Additionally, due to occasional solar-supported intensifying weather events, in Angot, Wadla, Daunt, Delanta, Mekdela, Wagdi, Kelala, Jama, Menzkiya, Moretina Jiru, Ensaro, Bidu, Kori, Dubti, Elidar, Mabey, Gimbichu, Adaa, Bishoftu, Akaki, Adama, Lome, Libenchkala, Dodota, Ziwai Dugda, Hitosa, Agraffe, Omobeyam, Yem, Gibe, Maji and Salamago will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.