Daily Weather Report 25 August 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ እና የተጠናከረ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያየዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው። በተጨማሪም ሰላሳ አራት በሚያህሉ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was strong and widspred cloud covers over the Kiremt rain benefiting areas. In this regard, many of their places received light to moderate (1-29 mm) rainfall amounts. Additionally, heavy rainfall was recorded exceeding 30 mm within a 24-hour in 34 stations.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ፤ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በፀሀይ ሀይል ታግዘው ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በአድዋ፣ እንዳባጻኀማ፣ ቀይሃተክል፣ በየዳ፣ ሰቆጣ፣ ላይጋይንት፣ ደራ፣ ፋርጣ፣ ዳንግላ፣ ቢዲዩ፣ ዱብቲ፣ ጎግ፣ አቦቦ፣ ዲማ፣ ወልበርግ፣ ዲንሾ እና ጎባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።
Tomorrow, Weather conditions conducive to the formation of Kiremt rain will continue over the Kiremt rain-benefiting areas of our country. In this regard, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; from Afar region Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones, from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, Gardula, Alle, Burji, Konso and Basketo zones and from Somali region Silte and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in most areas. Additionally, due to occasional solar-supported intensifying weather events, in Adwa, Endaba Tsahma, Keihatekel, Beyeda, Sekota, Laiygaint, Dera, Farta, Dangla, Bidiu, Dubti, Gog, Abobo, Dima, Wolberg, Dinsho and Goba will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.