Daily Weather Report 25 August 14

Weather Summary for previous day

Aug. 13, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አከባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው፡፡ በተጨማሪም በጭፍራ፣ መተከል፣ ነቀምቴ፣ ጭራ፣ ቀርሳ፣ መርሳ፣ ሞላሌ፣ ደራ፣ ጎብዬ፣ አንኮበር፣ ደጋአርቢ፣ እንደአባጉና እና ሀሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡

Yesterday, strong cloud coverage was observed over the parts of the country that benefit from the Kiremt rain. As a result, many areas that benefit from the Kiremt rain received light to moderate rainfall. Besides, Chifra, Metekal, Nekemte, Chira, Kersa, Mersa, Molale, Dera, Gobiye, Ankober, Dega Arbi, Endebaguna, and Haro received heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 15, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ፣ ጋቢ እና አዉሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን እና ቆራሄ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በፀገደ፣ ፀለምት፣ አሰገድ፣ ፂምቢላ፣ አሕፈሮም፣ አድዋ፣ ላዕላይ ማይጨው፣ ደባርቅ፣ በይዳ፣ ጃናሞራ፣ ሳሒላ፣ ዝቋላ፣ አባርጋለ፣ ሰቆጣ፣ ጓንጓ፣ ዳንግላ፣ አንካሻ፣ ወምበርማ፣ ቡሬ፣ ደምበጫ፣ ጃቢ ተህናን፣ ደብረኤሊያስ፣ ቡለን፣ ወንበራ፣ ዲባቴ፣ ዛዪ፣ ማኦኮሞ፣ ቤጊ፣ ባቦ፣ ጊዳሚ፣ አንፊሎ፣ ሳዮ፣ ጅማ ሆሮ፣ ዳሌዋበራ፣ ሳዲጨንቃ፣ ሀዋገላን፣ መቱ ዙሪያ፣ በሳለኖኖ፣ አሌ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ዋንታዎ፣ ኢታንግ፣ ጋምቤላ ዙሪያ እና መንገሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

For the upcoming day, widespread cloud coverage and accumulation will be present in the western, central, northeastern, and eastern parts of the country, which benefit from the Kiremt rain. In connection with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; the west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo national special none, north Shewa and Waghemra zones of Amhara region; Kilbeti, Fanti, Hari, Gabi and Awusi zones of Afar region; Metekal, Kamashi, Asossa and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones of Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa;: Majang, Nuwer, Itang and Agnuak zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones of the southwest Ethiopia region; Gurage, Silte, east Gurage, Marko special zone, Hadiya, Ye special zone, Kembata and Tembaro zones the central Ethiopia region; Walaita, Gofa, Basketo, south Omo and Gedeo zones of the south Ethiopia region; Sidama region zones and Siti, Fafen and Korahe zones of the Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, Tsegede, Tselemet, Asegede, Tsimbila, Ahferom, Adwa, Laelay Maichew, Debark, Beyida, Janamora, Sahila, Ziquala, Abergale, Sekota, Guangua, Dangila, Ankasha, Wemberima, Bure, Denbecha, Jabi Tehnan, Debre Elias, Bulen, Wenbera, Dibate, Zayi, Mao Komo, Begi, Babo, Gidami, Anfilo, Sayo, Jimma Horro, Dalewabera, Sadichenka, Hawagalan, Metu Zura, Salenono, Ale, Abobo, Lare, Wantao, Itang, Gambella Zura and Mengesh will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.