Daily Weather Report 25 August 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ ፅፅቃ፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ አምባማርያም፣ ስሪንቃ፣ ጨፋ፣ መሃልሜዳ፣ መካነሰላም፣ የትኖራ፣ ደብረብርሃን፣ እንዋሪ፣ ሾላገበያ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጨዋቃ፣ በደሌ፣ ነቀምቴ፣ ኢጃጂ፣ ሻምቡ፣ ካቺሴ፣ ወሊሶ፣ ቡኢ፣ ቁሉምሳ፣ ባቱ፣ ባሌሮቤ፣ አርሲ ሮቤ፣ ገለምሶ፣ ያቤሎ፣ ቦሬ፣ ቁልቢ፣ ሒርና፣ ደንገጎ፣ ላንጌ፣ ጎብይሬ፣ ቀርሳ፣ ካራሚሌ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባ፣ አሺ፣ ኦቦመሪጋ፣ ሙጊ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ ሲቦ፣ ቴፒ፣ ማሻ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሆሳዕና፣ ሰኮሩ፣ ብላቴ፣ ጅንካ፣ ሳውላ፣ ሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎንደር፣ አይከል፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጋምቤላ፣ ጅማ፣ አርባምንጭ እና መልካ ጀብዱ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the areas of our country that benefited from the winter rains. In this regard, in Mekelle, Tsitsika, Bahir Dar, Chagni, Mota, Debrework, Ambamariam, Srinka, Chefa, Mahmeda, Mekaneselam, Etonora, Debre Birhan, Enwari, Sholagebeya, Gore, Chira, Chewaka, Bedele, Nekemte, Ejaji, Shambu, Kachise, Woliso, Bui, Kulumsa, Batu, Balerobe, Arsi Robe, Gelemso, Yabelo, Bore, Kulbi, Hirna, Dengego, Lange, Gobyre, Kersa, Karamile, Bishoftu, Adama, Addis Ababa, Ashi, Obomeriga, Mugi, Satti Gebeya, Sibo, Tepi, Masha, Aman, Tercha, Hosanna, Sekoru, Bilate, Jinka, Saula, Hawassa and Wolayta Sodo they received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in nine areas of our country within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ እና የተጠናከረ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በመቀሌ፣ አይደር፣ አድርቃይ፣ ደባርቅ፣ ደብረታቦር፣ ደራ፣ ነፋስ መውጫ፣ አዴት፣ ሰከላ፣ ዳንግላ፣ ሰዴ፣ ደብረሲና፣ ሸኖ፣ ቱለፋ፣ ጨዋቃ፣ መኮ፣ በደሌ፣ ዶሪና፣ ጉሊሶ፣ መንዲ፣ ነጆ፣ ሲሬ፣ መርቲ፣ ሚኤሶ እና አዋሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።
Tomorrow There will be widespread and intensified cloud cover over the areas of our country that benefit from the kiremt rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo Nationality Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Benishangul Gumuz Region, Assosa, Mao Komo, Kamash and Metekel Zones; Gambella Region, Majang, Itang, Nuer and Anwuk Zones; Southwestern Ethiopia Region, Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; Central Ethiopia Region, Gurage, East Gurage, Kebena Special Zone, Marekko Special Zone, M' Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; Sidama Region zones, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardola, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopia Region; Hausi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar Region and Siti and Fafen zones of the Somali Region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, due to the intensifying weather events, Mekelle, Ayder, Adrakai, Debarq, Debre Tabor, Dera, Neifs Ntul, Adet, Sekela, Dangla, Sed, Debresina, Sheno, Tulefa, Salutka, Meko, Bedele, Dorina, Guliso, Mendi, Nejo, Sire, Merti, Mieso and Awash will experience heavy rainfall within 24 hours.