Daily Weather Report 25 August 07

Weather Summary for previous day

Aug. 6, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ አይደር፣ ጽጌሬዳ፣ ውቅሮማርየ፣ ውቅሮአምባ፣ እንዳባጉና፣ ጎንደር፣ ነፋስመውጫ፣ ሮቡገበያ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ደብረማርቆስ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ እንዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አሶሳ፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ኩሚ፣ መንገሽ፣ ኦቦመርጋ፣ ሲቦ፣ መንደር13፣ ይና፣ ኦሞናዳ፣ ያንፋ፣ ያዮ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ደምቢዶሎ፣ አንገርጉትን፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ሊሙገነት፣ በደሌ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ካችሴ፣ ኢጃጅ፣ ወሊሶ፣ ፊንጫ፣ አቃቂ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ሀሮዶየ፣ ላንጌ፣ ቦሬ፣ አዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታሶዶ፣ ምዕራብአባያ፣ ቢላቴ፣ ሳውላ፣ ዲላ እና አይሻ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም ሀያ በሚደርሱ አከባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a strong cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremt rains. In this regard, in Mekelle, Ayder, Tsigereda, Hukromarye, Hukromamba, Endabaguna, Gondar, Neifsmawcha, Robukeder, Adet, Mota, Debremarkos, Chagni, Dangla, Lalibela, Wogeltiye, Kombolcha, Chefa, Mekaneselam, Enwari, Debreberhan, Sholagebeya, Chafra, Semera, Gewane, Elidar, Asosa, Mankush, Bulen, Pawe, Gambella, Kumi, Mengesh, Obomerga, Sibo, Mender13, Yina, Omonada, Yanfa, Yayo, Nejo, Aira, Gimbi, Dembidolo, Angerguten, Chira, Jimma, Sokoru, Limugenet, Bedele, Gidaayana, Shambu, Kachse, Ijaj, Woliso, Fincha, Akaki, Kulmsa, Arsirobe, Gelemso, Harodoye, Lange, Bore, Addis Ababa, Bui, Endibar, Hosanna, Warabe, Hawassa, Wolaytasodo, West Abaya, Bilate, Saula, Dilla and Aisha they received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in about twenty areas within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 8, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ እንደሚስፋፉ እና እንደሚጠናከሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረና ፣ ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ቆላ ተምቤን፣ አቢአዲ፣ ሐገረሰላም፣ መተማ፣ ቋራ፣ ጉባ፣ ሰዴል፣ ወንበራ፣ ቡለን፣ ማንዱራ፣ አንጋሻ፣ አየሁ፣ ፍቼ፣ ያያ ጉለሌ፣ ቅምብቢት፣ እንዋሪ፣ በደሌ፣ ቦረቻ፣ ደዴሳ፣ አጋሮ፣ ቀርሳ፣ ጮራ፣ ወልበርግ፣ ሆሳዕና፣ አንገቻ፣ ብላቴ፣ ይርጋለም፣ ዲላ፣ ኮፈሌ፣ ዶዶላ፣ ሙኒሳ፣ ጎሎልቻ፣ መርቲ፣ ሴሩ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ እና አዲስአበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። ስለሆነም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አከባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡

Tomorrow Our numerical forecast data indicates that weather conditions favorable for the occurrence of kiremet rains will further expand and intensify in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale, Guj and West Guj zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Benishangul Gumuz Region: Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel Zones; Gambella Region: Majang, Itang, Nuer and Anuwak Zones; Southwestern Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; Central Ethiopia Region: Gurage, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; All zones of Sidama region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardola, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones of Southern Ethiopia region; Awsi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of Afar region and Siti and Fafen zones of Somali region will experience light to moderate rainfall at many places. In addition, due to the strengthening weather events, Kola Temben, Abiadi, Hagerselam, Metema, Qara, Guba, Sedel, Wenbera, Bulen, Mandura, Angasha, Ayehu, Fiche, Yaya Gulele, Qambit, Enwari, Bedele, Borecha, Dedesa, Agaro, Kersa, Chora, Wolberg, Hosanna, Angecha, Blate, Yirgalem, Dilla, Kofele, Dodola, Munisa, Gololcha, Merti, Seru, Bishoftu, Adama and Addis Ababa will experience heavy rainfall that may cause flash floods within 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute advises the community and relevant parties to take necessary precautions in flood-prone areas.