Daily Weather Report 25 August 06

Weather Summary for previous day

Aug. 5, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአድዋ፣ ሽሬእንደስላሴ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ሰንቃጣ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ መኾኒ፣ ውቅሮ፣ ማይሀንሳ፣ ጽጌሬዳ፣ ውቅሮማርየ፣ ውቅሮአምባ፣ ጎንደር፣ ነፋስመውጫ፣ ሮቡገበያ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ደብረማርቆስ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ እንዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፣ አሶሳ፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ኩሚ፣ መንገሽ፣ ኦቦመርጋ፣ ሲቦ፣ መንደር13፣ ይና፣ አማን፣ ኦሞናዳ፣ ያንፋ፣ ያዮ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ደምቢዶሎ፣ ጎሬ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ሊሙገነት፣ በደሌ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ካችሴ፣ ኢጃጅ፣ ወሊሶ፣ ፊንጫ፣ አቃቂ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ባቱ፣ አቦምሳ፣ መተሀራ፣ ገለምሶ፣ ሀሮዶየ፣ ላንጌ፣ ቦሬ፣ አዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታሶዶ፣ ምዕራብአባያ፣ ቢላቴ፣ ሳውላ፣ ዲላ እና አይሻ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በእንዳባጉና፣ ደንጎላት፣ መተማ እና ሻሁራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a strong cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In this regard, Adwa, Shireendusilassie, Axum, Adigrat, Senqata, Ayder, Maichew, Mekhoni, Hukro, Maihansa, Tsigereda, Hukromarye, Hukroamba, Gondar, Neifsmawcha, Robugebeya, Adet, Mota, Debre Markos, Chagni, Dangla, Lalibela, Wogeltiye, Kombolcha, Chefa, Mekaneslam, Enwari, Debre Birhan, Sholagebeya, Chafra, Semera, Gewane, Elidar, Asosa, Mankush, Bulen, Pawe, Gambella, Kumi, Mengesh, Obomerga, Sibo, Morgh13, Yina, Aman, Omonada, Yanfa, Yayo, Nejo, Aira, Gimbi, Dembidolo, Gore, Angerguten, Nekemte, Chira, Jimma, Sokoru, Limugenet, Bedele, Gidaayana, Shambu, Kachse, Ejaj, Wolisso, Fincha, Akaki, Kulmsa, Arsirobe, Batu, Abomsa, Metahara, Gelemso, Harodoye, Lange, Bore, Addis Ababa, Bui, Endibar, Hosanna, Warabe, Hawassa, Wolaytasodo, West Abaya, Bilate, Saula, Dilla and Aisha received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall of over 30 mm was recorded in Endabaguna, Dingolat, Metema and Shahura within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 7, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ታች እና ላይአርማጭሆ፣ ጉና በጌምድር፣ ላይጋይንት፣ ነፋስመውጫ፣ ሰዴሙጃ፣ ስማዳ፣ መቄት፣ ዳውንት፣ ላስታ፣ ላሊበላ፣ ጉባ ላፍቶ፣ መርሳ፣ አምባሰል፣ ኩታበር፣ ላጋምቦ፣ ወግዲ፣ ጃማ፣ ወረኢሉ፣ ጣርማበር፣ እንዋሪ፣ መራቤቴ፣ አንኮበር፣ ደብረ ወርቅ፣ መርጦለማርያም፣ እንማይ፣ እናርጅ እናውጋ፣ ስናን፣ ሸንዲ፣ ወንበራ፣ ደምበጫ፣ ቻግኒ፣ አንካሻ፣ ግምጃቤት፣ ማንዱራ፣ ቡለን፣ ጉባ፣ ጊዳአያና፣ ሊሙ፣ ሀሮሊሙ፣ ኢፋታ፣ አምቦ ዙርያ፣ ሊበን፣ ጃዊ፣ ጅባት፣ ወንጪ፣ አመያ፣ ደንዲ፣ ወሊሶ፣ ጮራ፣ ሊሙ ሴቃ፣ ቀርሳ፣ ሰኮሩ፣ ደዴሳ፣ እምድብር፣ ጉመር፣ ወልበርግ፣ አለታወንዶ፣ ቡፋሳ፣ ዶዶላ፣ ኮፈሌ፣ በቆጂ፣ አጋርፋ፣ ቢሾፍቱ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። ስለሆነም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አከባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡

Tomorrow our numerical forecast data indicates that weather conditions favorable for the formation of kiremet rains will intensify in the areas of our country that benefit from kiremt rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of the Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge and Bale, Guj and West Guj zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Majang, Itang, Nuer and Anuwak zones from Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; All zones of Sidama region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardola, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones of Southern Ethiopia region; Awsi, Kelbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of Afar region and Siti and Fafen zones of Somali region will receive light to moderate rainfall in many areas. In addition, due to the strengthening weather events, Tach and Lai Armachho, Guna Begemder, Laigaint, Neifsmuchha, Sedemuja, Smada, Meket, Daunt, Lasta, Lalibela, Guba Lafto, Mersa, Ambasel, Kutaber, Lagambo, Wagdi, Jama, Wereilu, Tarmaber, Enwari, Merabete, Ankober, Debre Work, Mertolemariam, Enmay, Enarj and Awga, Senan, Shendi, Wenerbera, Dembecha, Chagni, Ankasha, Gemjabet, Mandura, Bulen, Guba, Gidaayana, Limu, Harolimu, Ifata, Ambo Zuria, Liben, Jawi, Jibat, Wenchi, Amaya, Dendi, Woliso, Chora, Limu Seka, Kersa, Sekoru, Dedesa, Emdbir, Gumer, Wolberg, Aletwendo, Bufasa, Dodola, Kofele, Bekoji, Agarfa, Bishoftu and Addis Ababa will experience heavy rainfall that could cause flash flooding within 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute advises the community and relevant parties in flood-prone areas to take necessary precautions.