Daily Weather Report 25 August 05
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአድዋ፣ ሽሬእንደስላሴ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ሰንቃጣ፣ አጽቢ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ መሆኒ፣ ውቅሮ፣ ማይሀንሳ፣ ጽጌሬዳ፣ እንዳባጉና፣ ውቅሮማርየ፣ ውቅሮአምባ፣ ጎንደር፣ ነፋስመውጫ፣ አሸር፣ ሮቡገበያ፣ ቁንዝላ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ደብረማርቆስ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ አምባማርያም፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ መካነሰላም፣ እንዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ጭፍራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አሶሳ፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጉበቲ፣ ኩሚ፣ መንገሽ፣ ኦቦመርጋ፣ ሲቦ፣ መንደር13፣ ይና፣ ቴፒ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ኦሞናዳ፣ ያንፋ፣ ያዮ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ደምቢዶሎ፣ ጎሬ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ሊሙገነት፣ በደሌ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ካችሴ፣ ኢጃጅ፣ ወሊሶ፣ ፊንጫ፣ አቃቂ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ባቱ፣ አቦምሳ፣ መተሀራ፣ ገለምሶ፣ ሀሮዶየ፣ መቂ፣ ላንጌ፣ ቦሬ፣ ዶሎመና፣ መልካጀብዱ፣ ደንገጎ፣ ጃጃ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታሶዶ፣ ምዕራብአባያ፣ ቢላቴ፣ ሳውላ፣ ዲላ እና አይሻ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም መቀሌ፣ ደንጎላት፣ የጭላ፣ ደባርቅ፣ ሻሁራ፣ አባይሸለቆ፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ አምደወርቅ፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ ጨዋቃ፣ አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ አዲስአለም፣ ቁሉቢ፣ ካራሚሌ፣ ቀርሳ፣ ሂርና፣ ጨለንቆ፣ ሜኢሶ፣ ሐሮማያ እና የሪ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was strong cloud coverage over the Kiremt rainfall benefiting areas of our country. In this regard, Adwa, Shireendesilase, Axum, Adigrat, Sinkata, Atsebi, Aider, Maichew, Mehoni, Wukro, Wukromary, WukroAmba, Gondar, Nefasmewicha, Asher, Erobgebeya, Kunzla, Adet, Motta, Debre Markos, Chagni, Dangla, Lalibela, Wegeltena, Amba Mariam, Combolcha, Cheffa, Bati, Mekaneselam, Enwari, Debrebrihan, Sholagebeya, Chifra, Semera, Gewane, Elidar, Awasharba, Asossa, Mankush, Bullen, Pawe, Gambella, Fugnido, Gubeti, Kumi, Mengeshi, Obomerga, Sibo, Village13, Yina, Tepi, Aman, Tercha, Omonada, Yanfa, Yayo, Nedjo, Aira, Gimbi, Dembidolo, Gore, Angergutin, Nekemte, Chira, Jimma, Sokoru, Limugenet, Bedele, Gidayana, Shambu, Kachise, Ejaji, Woliso, Fincha, Akaki, Kulumsa, Arsirobe, Batu, Abomsa, Metehara, Gelemso, Harodoye, Meki, Lange, Bore, Dolomena, Melekjbidu, Dengego, Jaja, Harar, Dire Dawa, Addis Ababa, Bui, Emdibir, Hosanna, Werabe, Hawassa, Wolaitasodo, Mirabaya, Bilate, Sawla, Dilla and Aiysha received light to moderate (1-29 mm) amount of rainfall. Additionally, Mekelle, Dengolat, Yechila, Debark, Shahura, Abayshelleko, Bahir Dar, Debre Tabor, Amdework, Wereilu, Mehalmeda, Chewaka, Ambo, Bishoftu, Adama, AdisAlem, Kulubi, Karamile, Keresa, Hirna, Chellenko, Meiso, Haramaya, and Yeri heavy rainfall was recorded exceeding 30 mm within a 24-hour.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ፤ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በጣቁሳ፣ አለፋ፣ ጓንጓ፣ ወንበርማ፣ ደብረኤሊያስ፣ ሲያደብርና ዋዮ፣ ሞጃናወደራ፣ ጃዊ፣ ቡለን፣ ዛየ፣ ካማሽ፣ መዚንጋ፣ ኢባንቱ፣ ጊዳአያና፣ ኪረሙ፣ ጉዱሩ፣ አቤዶንጎሮ፣ አባቦ፣ ሊሙሰቃ፣ ጮራ፣ ኖኖ፣ ዳኖ፣ ኢሉገላን፣ ባኮቲቤ፣ ግንደበረት፣ ጮቢ፣ አምቦዙሪያ፣ ኢጄርሳላፎ፣ አመያ፣ ወንጭ፣ ሰደንሶዶ፣ ኩዩ፣ ያያጉለሌ፣ አበሽጌ፣ ቸሀ፣ እነሞር፣ ጊቤ፣ ጎምቦራ፣ ቦሎሶሶራ እና አቃቂ በ24 ሰዓት ውስጥ በረዶ የቀላቀለና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። ስለሆነም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አከባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡
Tomorrow, Weather conditions conducive to the formation of Kiremet rain will continue to more intensify over the Kiremt rain-benefiting areas of our country. In this regard, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge and Bale, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; from Afar region Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones and from Somali region Silte and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in most areas. Additionally, due to the intensifying weather events, Takusa, Alfa, Guangua, Wemberima, Debre Elias, SiadebrenaWayo, Mojana, Jawi, Bullen, Zaye, Kamash, Mezinga, Ibantu, Gidaayana, Kiremu, Guduru, Abadengoro, Ababo, Limuseka, Chora, Nono, Dano, Ilugelan, Bakotibe, Gundoberet, Chobi, Ambo Zuriya, Ijersalafo, Amaya, Sling, Sedensodo, Kuyu, Yayagulele, Abeshige, Cheha, Enemor, Gibe, Gombora, Bolososora, and Akaki are expected to experience significant rainfall that could lead to snowfall and flash flooding within 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute advises the community and relevant parties to take necessary precautions in flood-prone areas.