Daily Weather Report 25 August 04

Weather Summary for previous day

Aug. 3, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአድዋ፣ ሽሬእንደሥላሴ፣ አክሱም፣ ማይጨው፣ እዳጋአርቢ፣ ደንጎላት፣ ፣ውቅሮ፣ የጭላ፣ ማይሃንሰ፣ ውቅሮማሬ፣ ደባርቅ፣ አይከል፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ባህርዳር፣ አዴት፣ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ አዲስዘመን፣ ቡሬ፣ እብናት፣ ፈረስቤት፣ ኮሶበር፣ መካነእየሱስ፣ መርጦለማርያም፣ ሮቡገበያ፣ ሸንዲ፣ ደብረታቦር፣ ነፋስመውጫ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ ስሪንቃ፣ አምባማርያም፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ወረኢሉ፣ መካነሰላም፣ መሀልሜዳ፣ እንዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ጉንዶመስቀል፣ አዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ኢጃጅ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ጊምቢ፣ ጨዋቃ፣ አይራ፣ ደምቢዶሎ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ አጋሮ፣ ቢላምቢሎ፣ ቦርቃ፣ ሀሮ፣ ሸቤ፣ ያዮ፣ ኑራኤራ፣ አቦምሳ፣ ቁልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ባቱ፣ አደሌ፣ ፊንጫ፣ ጨፌዶንሳ፣ መቂ፣ አቃቂ፣ ገለምሶ፣ ሜኤሶ፣ ሂርና፣ ኩርፋጨሌ፣ ሐሮማያ፣ ጨለንቆ፣ ላንጌ፣ ቁሉቢ፣ መልካጀብዱ፣ ደንገጎ፣ ፣ ሰዲቃ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ አንጋጫ፣ ቦቃሶ፣ ዱራሜ፣ ጋምቤላ፣ አሽ፣ ባሮቦንጋ፣ ጭልቦ መንደር7፣ ጉበቲ፣ ኮበን፣ ኩሚ፣ ኦንጋ፣ ትንሹሜጢ፣ መንደር11፣ መንደር13፣ የሪ እና ይና ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቢሾፍቱ፣ ካቺስ፣ ጊዳአያና፣ ሊሙገነት፣ ቡኢ፣ ኩሚ፣ አዲስ አለም፣ አድርቃይ እና የሪ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a strong cloud cover over the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In this regard, Adwa, Shire enda Selassie, Axum, Maichew, Edaga Arbi, Dingolat, Hukiro, Yecla, Maihanse, Hugromare, Debark, Aikel, Chagni, Dangla, Bahir Dar, Adet, Mota, Debrework, Debremarkos, yetnora, Addiszemen, Bure, Ebnat, Feresbet, Kosober, Mekane Yesus, Mertole Mariam, Robukeder, Shendi, Debretabor, Neifsmawcha, Lalibela, Wogelte, Srinagar, Ambamariam, Kombolcha, Chefa, Wereilu, Mekaneselam, Mehalmeda, Enwari, Debrebirhan, Sholakeder, Gundomeskel, Addis Ababa, Ambo, Wolesi, Ijaj, Shambu, Nekemte, Gimbi, Saltuka, Aira, Dembidolo, Gore, Jimma, Limugenet, Agaro, Bilambilo, Borka, Haro, Shebe, Yayo, Nuraera, Abomsa, Qulmsa, Arsirobe, Batu, Adele, Fincha, Chefedonsa, Meki, Akaki, Gelemso, Mieso, Hirna, Kurfachele, Haromaya, Chelenko, Lange, Qulubi, Melkajebdu, Dengego, , Sedika, Enbir, Hosanna, Angcha, Bokaso, Durame, Gambella, Ash, Barobonga, Chlebo Village 7, Gubeti, Koben, Kumi, Onga, Meskhetemi, Village 11, Village 13, Yeri and Yina received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Bishoftu, Kachis, Gidaayana, Limugenet, Bui, Kumi, Addis Alem, Adrkai and Yeri received heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Aug. 5, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያእና፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የመኸር የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እንዲሁም ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖ እና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በዳውንት፣ መቅደላ፣ እንዋሪ፣ ሻምቡ፣ ቡሬ፣ መቱ፣ ጎግ፣ ጆሬ፣ አቦቦ፣ አኮቦ፣ መንገሽ፣ ከፋ፣ ዴቻ፣ አሌ፣ጋርዱላ፣ ጭሬ፣ አዳባ፣ ዶዶላ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። ስለሆነም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አከባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡

Tomorrow Weather conditions conducive to the formation of Kiremet rains will continue to intensify. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; ; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge and Bale, Guj and West Guj zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Benishangul Gumuz Region: Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel Zones; Gambella Region: Majang, Itang, Nuer and Anuwak Zones; Southwestern Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; Central Ethiopia Region: Gurage, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; The Hausa, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones of the Afar region and the Sitti and Fafen zones of the Somali region will receive light to moderate rainfall in most areas. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out harvest agricultural activities and for the provision of animal feed and drinking water for pastoral areas. Additionally, due to the intensifying weather events, Daunt, Mekdela, Enwari, Shambu, Bure, Metu, Gog, Jore, Abobo, Akobo, Mengesh, Kefa, Decha, Ale, Derashe, Chere, Adaba, Dodola and Addis Ababa will experience heavy rainfall that may cause flash floods within 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute advises the community and relevant parties to take necessary precautions in flood-prone areas.