Daily Weather Report 25 Apr 29

Weather Summary for previous day

April 28, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጊምቢ፣ አይራ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ አንገርጉትን፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ተርጫ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ዲላ፣ ቁሉቢ እና አዋሬ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሽላቦ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተሀራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ፣ ጎዴ እና ቀብሪዳሃር ከ36.0-42.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover over the southern, southwest, eastern, southeastern, and western parts of our country. In this regard, Gimbi, Aira, Gida'ana, Shambu, Angergutn, Limugent, Jimma, Bore, Negele, Tercha, Wolaytasodo, Sawla, Jinka, Dilla, Kulubi and Aware received light to moderate (1-29 mm) amounts of rain, while more than 30mm heavy amounts of rainfall were recorded in Shilabo. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded 36.0-42.0 degrees Celsius in Metema, Gambella, Fugnido, Metehara, Semera, Gewane, Awasharba, Aysha, Gode and Kebridahar.

Weather Forecast for next day

April 30, 2025

በነገዉ ዕለት ዝናብ ሰጪ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለም እና ምስራቅ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ማጃንግ እና ሊበን ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, rain-giving bring weather events will intensify in the Belg is main and second rain season areas and northwestern parts of our country. In association with this, from the Southwest Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Amaro, south Omo and Gedeo zones; from southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Oromia region; west Guji and Guji, Bale and east Bale, east and west Hararge, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Kelem, Horogudru, east and west Wellega, west, southwest and north Shewa zones; Addis Ababa; Harari; Dire Dawa; from Somali region: Siti, Fafen, Nogob, Liben, Dawa, Jarrar, Erer, Afder, Shebelle, Korahe and Doolo zones; Sidama region zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; from Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from Benishangul-Gumuz region: Metekel, Assosa, Kamash and Mao Como zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi, east and west Gojjam, north and south Wollo zones and from Tigray region northwest, west, east and central zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Kelem and East Wellega, Ilubabor, Jimma, Majang and Liben zones, they will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.