Daily Weather Report 25 Apr 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ጋምቤላ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ አርጆ፣ ጊዳአያና፣ ቡሬ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ተርጫ፣ አማን፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ቢላቴ፣ ሐዋሳ፣ ሆሳዕና፣ ነገሌ፣ ጎዴ፣ ጅግጅጋ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ሻሁራ እና አይከል ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎሬ እና በቦሬ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ እና ቀብሪዳሃር ከ36-42 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the southwestern, south, southeastern, and northwestern areas of our country had cloud coverage. Consequently, Lare, Fugnido, Gambella, Gimbi, Aira, Arjo, Gidayana, Bure, Bedele, Gatira, Chira, Limugenet, Jimma, Tercha, Aman, Sawula, Jinka, Bilate, Hawassa, Hosaina, Negele, Gode, Jigjiga, Chagni, Dangila, Shahura, and Ayikel received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, more than 30 heavy rainfalls were recorded in Gore and Bore. In contrast, the maximum temperature of the day was recorded in Metema, Gambella, Fugnido, Metehara, Dire Dawa, Aisha, and Kebridehar between 36-42 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ ኤረር እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሸካ፣ ቄለም፣ ኢሉባቦር እና ጅማ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በአቦቦ፣ ላሬ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ሚሌ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
For the next day, cloud coverage is anticipated over areas typically experiencing the Belg main and second rainy season, as well as northwestern parts of the country. In this respect, from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, south Omo and Gedeo zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro; from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, west and south west Shewa zones; Dire Dawa; Harar; Zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Dollo, Jarar, Nogob, Erer and Fafen zones; from central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Majang and Itang zones; from Amhara region north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Asosa and Mao Komo zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, Sheka, Kelam, Ilubabor, and Jimma zones will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, the maximum daily temperature will be recorded exceeding 38 degrees Celsius in Abobo, Lare, Gambella, Fugnido, Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Mile, Awash Arba, Gewane, and Gode.