Daily Weather Report 25 Apr 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በምስራቅ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ኮንሶ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ፣ ዲላ፣ ሀመሮ፣ ጅግጅጋ፣ ግራዋ፣ ጎብየሬ፣ ሽላቦ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ሊሙገነት፣ ጊምቢ፣ ጎሬ፣ ጨዋቃ፣ ነቀምቴ እና ደብረወርቅ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተሀራ፣ ሜኢሶ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southwest, south, east, west and northwestern parts of our country. In this regard, Konso, Jinka, Arba Minch, Dilla, Hamero, Jigjiga, Grawa, Gobyere, Shilabo, Bulehora, Negele, Limugenet, Gimbi, Gore, Chewaka, Nekemte and Debrework received light to moderate amounts (1-29 mm) of rain. On the other hand, in Metehara, Meiso and Gode the maximum temperature of the day in was recorded as 35.0-38.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ሐረሪ፣ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብና ምዕራብ ትግራይ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአፍዴር፣ ሸበሌ፣ ሸካ እና ጅማ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be strong cloud cover over the of southern, southeastern, southwest and eastern Belg rainy season benefiting areas of our country, as well as the western and northwestern parts of the country. In association with this, from the South Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Amaro, South Omo and Gedeo zones; from the Southwest Ethiopia region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; Southwest Ethiopia region; west Guji and Guji, Bale and east Bale, east and west Hararge, west Arsi, Jimma, Ilubabor, Kelem, Horogudru, east and west Wellega, west and southwest Shewa zones; Harari, Dire Dawa; from Somali region: Fafen, Liben, Jarrar, Erer, Afder, Shebelle, Korahe and Doolo zones; Sidama regional zones; from Gambella Region of Agnwuak, Nuer, Itang and Majang zones; Central Ethiopia region: Gurage, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; Benishangul-Gumuz region: Metekel, Assosa, Kamash and Mao Como zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi, east and west Gojjam zones, and Tigray region northwest and west zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Afder, Shebelle, Sheka and Jimma zones, they will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the maximum temperature for the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.