Daily Weather Report 25 Apr 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በቴፒ፣ በጎሬ፣ በቦሬ እና በቡሌሆራ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቦባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎድ እና ጨዋቃ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.0-41.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southwest, south and northwest areas of our country. Along with this, light to moderate amounts of rainfall were recorded in Tepi, Gore, Bore and Bulehora. On the other hand, in Metema, Metehara, Dire Dawa, Gode and Chewaka, the maximum temperature of the day was recorded as 37.0-41.5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ ሊበን፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ አፍዴር እና ዶሎ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ የካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ እና በዶሎ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation over the main and second Belg rainy season benefiting areas, as well as the northwest parts of the country. In association with this, from the South Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, South Omo and Gedeo; from southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Oromia region Guji and west Guji, Borena, Bale and east Bale, west and east Hararge, Arsi and west Arsi, west Shewa, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, west and east Wellega zones; Addis Ababa; from Somali region Fafen, Siti, Jarrar, Erer, Nogob, Liben, Korahe, Shebelle, Afder and Doolo zones; Sidama region zones; from Central Ethiopia region Hadia, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; from the Gambella region, Agnuak, Itang and Majang zones; from Amhara region, Central and west Gondar, Awi and west Gojjam zones; From Benishangul-Gumuz region, Metekel, Kamash, Asossa and Mao Como will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Sheka and Doolo zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quarry, Metekel, Gambella, Lare, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.