Daily Weather Report 25 Apr 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በቡሬ፣ በአርጆ፣ በሐረር፣ በቴፒ፣ በዲላ እና በአሶሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ዝናብ ያገኙ ሲሆን በጋምቤላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ እና ፓዌ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southwest, west and east parts of our country. Along with this, light to moderate amounts of rainfall were recorded in Bure, Arjo, Harar, Tepi, Dilla and Assosa, while heavy amounts of more than 30mm were recorded in Gambella within 24 hours. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Gewane, Semera and Pawe, the maximum temperature of the day was recorded as above 38 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ሐረሪ፣ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ የም ልዩ ዞን እና ከምባታ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern, southeastern, southwest eastern Belg rainy benefiting areas of our country, as well as the western and northwestern parts of the country. In association with this, from the Southwest Ethiopia region Welayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Amaro, South Omo and Gedeo zones; from southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Oromia region west Guji and Guji, Bale, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Kelem, Horogudru, east and west Wellega zones; Harari, Dire Dawa; From the Somali region Fafen, Liben, Afder, Shebelle, Korahe and Doolo; Sidama region zones; from the Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; from the Central Ethiopia region Hadiya, Yem Special zone and Kembata zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa, Kamashi and Mao Como zones, and from the Amhara region west and central Gondar, Awi and west Gojjam zones. On the other hand, forecast information show that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.