Daily Weather Report 25 Apr 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘም መተከል፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ዲላ፣ ነገሌ እና አርሲ ሮቤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝቷል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፤ አይሻ እና ገዋኔ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud coverage over the southern, southwestern and western parts of our country. In connection with this, Metekel, Gambella, Fugnido, Dilla, Negele and Arsi Robe received light to moderate rain. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Gambella, Fugnido; Aisha and Gewane.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ እንዲሁም ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጌዲኦ እና ጎፋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የአፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡በሌላ በኩል በመተማ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ጋምቤላ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern, southeastern, southwestern, which benefit from the belg rains and western regions of our country. In this regard, Bench Sheko, Sheka, and Kefa zones of the southwestern Ethiopian region; Gedio, Wolaita and Gofa zones zone of the southern Ethiopian region; Sidama region zones; Afder and Shebele zones of the Somali region; Buno Bedele, Ilubabor, Kelem and West Wellega, West and East Hararge, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji and Borena zones of the Oromia region; Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones of the Gambella region; West Gondar Zone of the Amhara Region and Metekel, Kemash, Asossa and Mao Komo Zones of the Benishangul Gumuz Region will experience light to moderate rainfall. On the other hand, the forecast data shows that the maximum temperature of the day will be above 38 degrees Celsius in Metema, Lare, Fugnido, Gambella, Semera, Dubti, Gewane and Kebridehar.