Daily Weather Report 25 Apr 23

Weather Summary for previous day

April 22, 2025

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በአርባምንጭ፣ ወላይታሶዶ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጂንካ፣ ብላቴ፣ ሀዋሳ፣ አይራ፣ አርሲሮቤ፣ አደሌ፣ ባሌሮቤ፣ ነገሌ፣ ቦሬ፣ ገለምሶ፣ ሐሮማያ፣ ሂርና፣ ሐረር፣ ቁሉቢ፣ ደንገጎ፣ ዶሎኦዶ፣ ደብረብርሀን፣ መሀልሜዳ እና አዋሽአርባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የተመዘገበባቸው ሲሆን በሳውላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ አዋሽአርባ እና መተሀራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36-43 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the Belg rain benefiting areas of our country. In this regard, in Arbaminch, Wolaytasodo, Mirab Abaya, Jinka, Bilatte, Hawassa, Aira, Arsi Robe, Adelle, Bale Robe, Negele, Bore, Gemelso, Haramaya, Hirna, Harar, Kulubi, Dengego, Doloodo, Debre Birhan, Mehalmeda and Awasharba recorded light to moderate amounts of rain, while heavy amounts of more than 30mm were recorded in Sawla within 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded 36-43 degrees Celsius in Metema, Gambella, Fugnido, Gewane, Semera, Awasharba and Metehara

Weather Forecast for next day

April 24, 2025

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን ዳዋ፣ አፍዴር፣ ኖጎብ እና ሸበሌ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second Belg rainy season benefiting areas, as well as the northwest parts of the country. Along with this, from Southern Ethiopia region Basketo, south Omo and Gedeo zones; Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa and west Omo zones; from Oromia region west Guji, Bale, east Hararge, Jimma, Ilubabor, Kelem and west Wellega zones; from Somali region Liben, Dawa, Afder, Nogob and Shebelle zones; Sidama region zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones, from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa and Mao Como zones and from Amhara region west Gondar and North Shewa zones will receive light amounts of rainfall. On the other hand, forecast information show that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.