Daily Weather Report 25 Apr 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በምስራቅና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ሐረር፣ ኩርፋጨሌ፣ ሐሮማያ፣ አደሌ፣ ነገሌ፣ ቦሬ፣ ዶሎኦዶ፣ ጎንደር እና ደባርቅ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southern, eastern, and northwestern parts of our country. In association with, Harar, Kurfachele, Haramaya, Adelle, Negele, Bore, Doloodo, Gondar and Debark received light to moderate amounts of rain. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Gambella, Fugnido, Semera, Gewane and Awash Arba.
Weather Forecast for next day
በነገው በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern, southeastern, and southwestern Belg rainy benefiting areas of our country, as well as the west and northwestern parts of the country. Along with this, the Southern Ethiopia region Basketo, Amaro, South Omo and Gedio zones; from the Southwest Ethiopia region: Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and west Omo zones; From Oromia region: Guji and, west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Kelem and west Wellega zones; from Somali region Liben zone; Sidama region zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; from Amhara region west Gondar zone and from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa and Mao Como zones will receive light amounts of rainfall. On the other hand, forecast data shows that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Semera, Dubti, Gewane and Awash Arba.