Daily Weather Report 25 Apr 21
Weather Summary for previous day
ባለፉት ሶስት ቀናት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜን የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ኮንሶ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ የማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቦሬ እና ቴፒ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተከል፣ አይሻ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪዳሃር እና ጋምቤላ ከ35-42.7 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Over the past three days, there has been cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg and the northern parts of our country. In this regard, the Borena and East Borena, West Guji, Arsi, Jimma, Ilubabor, North, West, South West and East Shewa zones; Wolaita, Gamo, Gofa and Konso zones; Gurage, Hadiya and Silte zones; Central and South Gondar, East Gojam, South Wollo and North Shewa zones; South East and East Tigray zones and Sidama region zones received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall of over 30mm was recorded in Bore and Tepi. On the other hand, the highest daily temperatures were recorded in Metekel, Aisha, Fugendo, Kebridehar and Gambella, ranging from 35-42.7 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ ማኦ ኮሞ እና አሶሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ እና ሸርኮሌ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of our country. In connection with this, the Wolaita, Gofa, Gamo, Burji, Konso, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, East and West Hararge, Ilubabor, West and Kelem Wellega, Sidama Region zones; Dawa, Liben, Afder and Shebele zones of Somali Region; Anuak and Majang zones of Gambella Region and Metekel, Mao Komo and Asosa of Benishangul Gumuz Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, our statistical forecast data indicates that the daily maximum temperature will be above 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugendo and Sherkole.