Daily Weather Report 25 Apr 17

Weather Summary for previous day

April 16, 2025

በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽላቦ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ቦሬ፣ ሂርና፣ መተሀራ፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ አንገርጉትን፣ ጊምቢ፣ ጉንዶመስቀል፣ ሐረር፣ ሀዋሳ፣ ብላቴ፣ ዲላ፣ ወላይታሶዶ፣ አርባምንጭ፣ ሳውላ፣ ምዕራብአባያ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ተርጫ፣ ጋምቤላ፣ ጎንደር፣ ቻግኒ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ላሊበላ እና አምባማርያም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የተመዘገበባቸው ሲሆን በባሌሮቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ እና ቀብሪዳሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-39.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover over the main and second Belg rainy season benefiting areas of the country. In association with, light to moderate amounts of rainfall were recorded in Shilabo, Negele, Moyale, Yabelo, Bore, Hirna, Metehara, Arjo, Gore, Angergutin, Gimbi, Gundomeskel, Harar, Hawassa, Bilate, Dilla, Wolaitasodo, Arba Minch, Sawla, Mirababaya, Jinka, Konso, Burji, Tercha, Gambella, Gondar, Chagni, Adet, Motta, Debre work, Debre Markos, Yetnora, Lalibela and Amba Mariam, while heavy amounts of more than 30mm were recorded in Bale Robe in 24 hours. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Semera, Gewane, Awasharba and Kebridehar recorded the highest temperature of the day at 36.0-39.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

April 18, 2025

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ አፍዴር እና ዶሎ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Tomorrow, there will be strong cloud cover over the main and second Belg rainy season benefiting areas, as well as the northwest parts of the country. Along with this, from the Southwest Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, South Omo and Gedeo zones; Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; From Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, west and east Hararge, west Arsi, west, Southwest and east Shewa, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Kelem, Horo Guduru, west and east Wellega, zones; Addis Ababa; Somali region: Fafen, Jarrar, Erer, Nogob, Korahe, Afder and Doolo zones; Sidama regional zones; Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; west, northwest and central zones of Tigray region; from Amhara region central, north and south Gondar, Awi Zone, West and East Gojjam, Waghemra and North Wollo zones; from Benishangul-Gumuz region of Kamash, Asossa and Mao Como zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, Sheka and west Omo zones will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, forecast information show that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Semera, Dubti, Gewane and Awash Arba.