Daily Weather Report 25 Apr 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ የሊበን፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ጃራር እና ፋፈን ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ኮንሶ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ የማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በካቺስ፣ ሰኮሩ፣ ካራሚሌ፣ ጨለንቆ እና ተልተሌ ከ30 እስከ 101.2 ሚ.ሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪዳሃር እና ጋምቤላ ከ35-39 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a strong and widespread cloud cover over the main and second rainy seasons of the Belg. In this regard, the Borena and East Borena, West Guji, Arsi, West and East Hararge, Jimma, Ilubabor, North, West, South West and East Shewa zones; Liben, Shebelle, Korahe, Jarar and Fafen zones; Wolaita, Gamo, Gofa and Konso zones; Gurage, Hadiya and Silte zones; Central and South Gondar, East Gojam, South Wollo and North Shewa zones; South East and East Tigray zones; Harar; Dire Dawa and Sidama regional zones received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of 30 to 101.2 mm was recorded in Kachis, Sokoru, Karamile, Chelenko and Teltele.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜን የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ ዶሎ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ጅማ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ፣ አፍዴር፣ ጉጂ፣ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ አዋሽ አርባ እና ገዋኔ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for the occurrence of belg rains will continue to intensify in the main and second rainy seasons of belg and in the northern regions of our country. In this regard, the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; From the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, East and West Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru and East Wellega, North, West, South West and East Shewa zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Sidama Region zones; From the Somali Region, Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer, Siti, Fafen, Doolo and Jarar zones; The Central Ethiopian Region's Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; the Gambella Region's Anuak and Majang zones; the Tigray Region's West, Northwest, Central and Southeast zones; and the Amhara Region's North, Central and South Gondar, West and East Gojam, North and South Wollo, and Waghemra zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, Jimma, Kefa, West Omo, Sidama, Wolaita, Gamo, South Omo, Konso, Afder, Guji, and West Guji zones will experience heavy rainfall that could cause flash flooding within 24 hours. On the other hand, our statistical forecast data indicates that the maximum daily temperature will be above 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Awash Arba and Gewane.