Daily Weather Report 25 Apr 15

Weather Summary for previous day

April 14, 2025

በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ጅማ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ ቡርጂ እና ኮንሶ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ምስራቅ ትግራይ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም ስሪንቃ፣ካራሚሌ ፣አምቦ፣ ታርጫ፣ጃራ፣ጊኒር እና በዲላ ከ30 እስከ 50.2 ሚ.ሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ፉኝዶ፣ጋምቤላ፣አቦቦ፣ ድሬዳዋ እናጎዴ ከ36.2-37.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday strong widespread cloud cover over parts of our country that were Belg is their main and second rainy season. In line with this Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, North, West and East Shewa Zones, Siti and Fafen Zones; Wolayita, Gamo, Gofa, Burji and Konso Zones; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; East Gojjam, South and North Wollo and North Shewa Zones; East Tigray Zone and Sidama Regional Zones they received light to moderate (1-29 mm) amounts of rain. In addition, Sirinka , Kara mile, Ambo, Tercha, Jara, Ginir and Dilla received heavy amounts of rainfall of 30 to 50.2 mm. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Fugnedo, Gambella, Abobo, Dire Dawa and Gode at 36.2-37.2 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

April 16, 2025

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በተለይም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ እና ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን፣የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ዶሎ እና ጃራር ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር ፣ጃራር ፣ምስራቅ ሐረርጌ፣ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ጅማ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንታ፣ደቡብ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በአቦቦ፣ ላሬ፣ ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ጋምቤላ፣ ሰመራ፣ ድሬዳዋ፣ዱብቲ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will have widespread and strong cloud cover over areas of the country, especially in the south, southwest and southeast, as well as northwestern parts of the country, which are Belg is their main and second rainy season there will be widespread and strong cloud cover .In line with this from Central Ethiopia region of Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones;from south Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, South Omo and Gede’o zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones of the Southwest Ethiopia region; from the Oromia region of Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, East and West Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West, Southwest and East Shewa Zones; Addis Ababa; Sidama Regional Zones; from Somali Region: Fafen, Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer, Dolo and Jarar Zones; Agnuak and Majang zones of Gambella Region; Central Zone of Tigray Region; from Amhara Region West, North, Central and South Gondar, West and East Gojjam, North and South Wollo, Waghemra, Oromo Nation Special Zone. In addition, in Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer, Jarar, East Hararge, Bale, Guji and, West Guji, Jimma, Wolayita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, Konta, South and West Omo zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day will be recorded as above 38 degrees Celsius in Abobo, Lare, Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Semera, Dire Dawa, Dubti, Awash Arba, Gewane and Gode.