Daily Weather Report 25 Apr 14

Weather Summary for previous day

April 13, 2025

በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን ክፍሎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ የሊበን፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ጃራር እና ፋፈን ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ኮንሶ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ የማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሞያሌ፣ ቦሬ፣ ቀብሪዳሃር፣ ባቱ፣ አርሲሮቤ፣ ቡኢ፣ አዳማ፣ እና የትኖራ ከ30 እስከ 92 ሚ.ሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ፣ ፉኝዶ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪዳሃር ከ35-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, strong and widespread cloud coverage was observed over areas where the Belg is the main and second rainy season of the country. Consequently, Borena and east Borena, west Guji, Arsi, west and east Hararge, Jimma, Ilubabor, north, west, south west and east Shewa zones; Liben, Shebelle, Korahe, Jarar and Fafen zones; Walaita, Gamo, Gofa and Konso zones; Gurage, Hadiya and Silte zones; central and south Gondar, east Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; south east and east Tigray zones and Sidama region zones received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, Moyale, Bore, Kebridahar, Batu, Arsirobe, Bui, Adama, and Yetnora received heavy rainfall ranging from 30 to 92 mm. In contrast, the maximum daily temperature was recorded in Metema, Fugnido, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebridahar, ranging from 35 to 41 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

April 15, 2025

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በተለይም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት የሚኖራቸው ሲሆን፤ በሰሜን የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ ዶሎ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀሪ እና ጋቢ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ጃራር፣ ኤረር፣ አፍደር፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ጅማ፣ ከፋ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ደራሼ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረውም የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በአቦቦ፣ ላሬ፣ ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

For the upcoming day, areas where Belg is the primary and second rainy season, particularly in the south, southwest, and southeast of the country, will have strong cloud coverage and accumulation; additionally, there will be cloud coverage in the northern parts. In this respect, from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, south Omo and Gedeo zones; from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Sidama region zones; from Somali region Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer, Siti, Fafen, Dollo and Jarar zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak and Majang zones; from Tigray region west, northwest, central and southeast zones; from Amhara region north, central and south Gondar, west and east Gojjam, north and south Wollo, Waghemra, Oromo ethnic special zone and north Shewa zones; from Afar region Hari and Gabi zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, Jarar, Erer, Afder, east Hararge, Arsi, Jimma, Kefa, Walaita, Gamo, south Omo, Konso, Burji, Amaro, and Derashe zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours; the amount and distribution of rainfall will be crucial for Belg agricultural activities. Conversely, the maximum temperature of the day will be recorded exceeding 38 degrees Celsius in Abobo, Lare, Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Awash Arba, Gewane, and Gode.