Daily Weather Report 25 Apr 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆንና፤ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ ለአብነትም በሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ ባሌሮቤ፣ አርሲሮቤ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ጂንካ፣ ዲላ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሽላቦ፣ ጎዴ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆ፣ ሂርና፣ ጎብየሬ፣ ጅግጅጋ፣ ሃርሽም፣ ሀመሮ፣ ጉናጌዶ፣ ወራቤ፣ እምድብር፣ ጅማ፣ ጎሬ፣ አርጆ፣ ግምቢ፣ ነቀምቴ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ አቦምሳ፣ አዲስ አበባ፣ እነዋሪ፣ መካነሰላም፣ ደብረማርቆስ፣ መሀልመዳ፣ ማጀቴ፣ ባቲ፣ ሲሪንቃ እና መቀሌ ዝናብ ተመዝግቦባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኢጃጂ፣ ቡኢ፣ ሆሳዕና እና ተርጫ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በአዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ፉኝዶ ከ35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, widespread cloud coverage was observed over the areas where the Belg is the country's primary and second rainy season portion, and many areas received light to moderate rainfall. Thus, Moyale, Yabelo, Bore, Bulehora, Bale Robe, Arsi Robe, Burji, Konso, Jinka, Dilla, Hawasa, Walaita Sodo, Shilabo, Gode, Kulubi, Chelenko, Hirna, Gobiyare, Jigjiga, Harshim, Hamero, Gunagedo, Werabe, Emdibir, Jima, Gore, Arjo, Gimbi, Nekemte, Bishoftu, Adama, Abomsa, Addis Ababa, Enewari, Mekaneselam, Debremarkos, Mehalmeda, Majete, Bati, Sirinka and Mekelle rain was recorded. Additionally, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Ejaji, Bui, Hosana, and Tercha. On the other hand, the day's maximum temperature was recorded above 37 degrees Celsius in Awash Arba, Gode, and Fugnido.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜን የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ፋፈን እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀሪ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ቂልበቲ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ሸዋ፣ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ሀድያ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረውም የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud cover and accumulation over the main and second rainy seasons of the Belg and the northern parts of the country. In this regard, the zones of Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, South Omo and Gedeo of the Southern Ethiopian Region; the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro of the south west Ethiopian region; the zones of Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi East and West Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, West and East Wellega, North, West, South West and East Shewa zones of the Oromia Region; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; the zones of Sidama Region; From the Somali Region: Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer, Fafen and Jarar Zones; From the Central Ethiopia Region: Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; From the Gambella Region: Agnuak and Majang Zones; From the Benishangul Gumuz Region: Mao Komo and Kamash Zones; From the Tigray Region: West, North West, Central, South East and East Zones; From the Amhara Region: North, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, North and South Wollo, Waghemra, Oromo Special Zone and North Shewa Zones; In the Afar region, Hari, Gabi, Fanti, Awusi and Kilbeti zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, East Gojam, West Shewa, Bedele, Ilubabor, Jimma, Sheka, Kefa, Hadiya, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, West and South Omo zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours; the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, the maximum temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Humera, Metema, Quara, Semera, Dubti, Awash Arba, Gewane, and Gode.