Daily Weather Report 25 Apr 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን ክፍሎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ስለሆነም በሳዉላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ምዕራብ አባያ፣ ተርጫ፣ ቢላቴ፣ ሐዋሳ፣ ነገሌ፣ ባሌሮቤ፣ አርሲሮቤ፣ ወሊሶ፣ ካቺሴ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ሊሙገነት፣ ጎሬ፣ ጨዋቃ፣ ወራቤ፣ እምድብር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ነፋስመዉጫ፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ መካነሰላም እና አለምከተማ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጂንካ፣ በአማን፣ በአርባ ምንጭ እና በአንገርጉትን ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በጋምቤላ፣ ፉኚዶ፣ መተማ፣ ኑራኤራ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ከ37 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, widespread cloud coverage was observed over the areas where the Belg is the country's primary and second rainy season portion. Thus, Sawula, Walaita Sodo, Mirab Abaya, Tercha, Bilate, Hawassa, Negele, Balerobe, Arsirobe, Woliso, Kachise, Jimma, Chira, Limugenet, Gore, Chewaka, Werabe, Emdibir, Gambella, Fugnido, Gondar, Ayikel, Bahirdar, Dangila, Nefasmewcha, Debrework, Debremarkos, Yetnora, Mekaneselam and Alemketema received light to moderate rainfall. Additionally, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Jinka, Aman, Arba Minch and Angergutin. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 37 degrees Celsius in Gambella, Fugnido, Metema, Nuraera, Dire Dawa, Metehara, Gewane and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ፋፈን፣ ጃራር እና ሲቲ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀሪ እና ጋቢ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳዉሮ እና ጎፋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረውም የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ ማንኩሽ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
For the upcoming day, weather conditions favor rain formation will continue to intensify in areas where the Belg is the main and second rainy season, as well as in the north and northwest parts of the county. Consequently, from south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, south Omo and Gedeo zones; from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, west, south west and east Shewa zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Somali region Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Dollo, Nogob, Erer, Fafen, Jarar and Siti zones; zones of Sidama region; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Itang and Majang zones; from Benishangul Gumuz region Asosa, Mao Komo and Kamashi zones; from Amhara region north, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, Waghemra and north Shewa; from Tigray region west, north west, central, south east and east zones; from Afar region Hari and Gabi zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Besides, the Buno, Bedele, Ilubabor, Jimma, Sheka, Kefa, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and Gofa zones are expected to receive over 30 mm of heavy rainfall in 24 hours; the amount and distribution of rainfall will be crucial for Belg agricultural activities. Conversely, the maximum daily temperature will be recorded above 38 degrees Celsius in Metema, Quara, Mankush, Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Semera, Gewane, Awash Arba, and Gode.