Daily Weather Report 25 Apr 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዞም በቻግኒ፣ ጊዳ አያና፣ ነጆ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ አርጆ፣ ጊምብ፣ ደንቢ ዶሎ፣ ጭራ፣ ጋምቤላ፣ ሞያሌ፣ ነገሌ እና ዶሎ ኦዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቡለን ከባድ መጠን ያለዉ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኝዶ፣ ጎዴ፣ ገዋኔ እና ሰመራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the northwest, east, central, southeast, southwest and southern parts of our country. In addition, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Chagni, Gida Ayana, Nedjo, Aira, Nekemte, Bedele, Arjo, Gimbi, Dembi Dolo, Cira, Gambella, Moyale, Negele and Dolo Odo, while heavy rainfall was recorded in Bullen. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Gambella, Fugnido, Gode, Gewane and Semera.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ኦሮ ጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል የኑዌር፣ ኢታንግ፣ ማጃንግና አኙዋክ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ሊበን፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ዶሎ፣ ዳዋ እና አፍዴር ዞኖች፤ እንዲሁም ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ መተከል፣ ጉራጌ እና ሀድያ ዞኖች በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በዱብቲ፣ ሰመራ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ ቋራ እና ሁመራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For tomorrow Weather conditions favorable for rains will continue to intensify in the main and second rainy seasons of the Belg, as well as in the northern and northwestern regions of our country. In this regard, from the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones; from the Central Ethiopian Region, Gurage, Hadiya, Halaba, Silte, and the Special Zone; from the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gofa, Basketo, Gamo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, Gedeo and South Omo zones; From the Oromia Regional State, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Oro Guduru, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, East Hararge, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; from the Tigray region Central, Northwestern and Western zones; Dire Dawa, Harar; Sidama region zones; Nuer, Itang, Majang and Agniwak zones of Gambella region; Fafen, Jarar, Erer, Liben, Korahe, Nogob, Dolo, Dawa and Afder zones of Somali region; Central, North, West and South Gondar, Awi zone, West and East Gojam zones of Amhara region; and Asossa, Metekel, Kemash and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Central Gondar, Awi zone, Metekel, Gurage and Hadiya zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature will exceed 38 degrees Celsius in Dubti, Semera, Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Metema, Quara, and Humera.