Daily Weather Report 25 Apr 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ በመሆኑም በጅማ፣ አርጆ፣ ሊሙገነት፣ ቡሬ፣ ጋምቤላ፣ ጃራ፣ ባሌሮቤ፣ ዶሎመና፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ፣ ጂንካ፣ ዲላ፣ ብላቴ፣ ቡርጂ ደባርቅ፣ መተማ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ አዴት፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ መተከል እና አሶሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ የነበራቸው ሲሆን ያቤሎ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በአይሻ፣ ፉኝዶ እና መተማ ከ36-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the was the cloud coverage over western, southern and northwest parts of the countries. In addition to this In Jimma, Arjo, Limugenet, Bure, Gambella, Jara, Bale Robe, Dolo Mena, Negele, Hawassa, Wolaita, Jinka, Dilla, Burji, Debark, Metema, Gonder, Aykel, Adet, Chagni, Metekel and Assosa there was light rain. On the other hand daily maximum temperature of Ayesha, Fugnido and Metema from 36-41 recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋናኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ፤ ደቡብ ምስራቅ እና በሰሜን ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የተስፋፋ የደመና ሽፋን እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የአፍዴር፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36-38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow Forecast data shows that there will be widespread cloud cover in the southern, southeastern, northeastern, and western regions of our country, which are the main and second rainy seasons of the belg. Therefore, from the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, South Omo and Gedio zones; from the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; from the Oromia Region, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, West Arsi zones; The Afder, Liben and Dawa zones of the Somali Region; the Sidama Region zones; the Anuak and Majang zones of the Gambella Region; the West, Central and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam zones of the Amhara Region; and the Metekel, Asosa and Mao Komo zones of the Benishangul Gumuz Region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm); the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out autumn agricultural activities. On the other hand, the highest daily temperatures in Humera, Metema, Gambella, Lare, Fugendo, Semera, Gewane, Awash Arba and Gode will be recorded above 36-38 degrees Celsius.