Daily Weather Report 25 Apr 07

Weather Summary for previous day

April 6, 2025

በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜንና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአፅቢ፣ አይደር፣ ደባርቅ፣ መተማ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ደብረታቦር፣ ነፋስመዉጫ፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና፣ አምባማሪያም፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ደብረማርቆስ፣ ጉንዶመስቀል፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ጨዋቃ፣ አንገርጉትን፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ጭራ፣ ሆሳዕና፣ ሐዋሳ፣ ቢላቴ፣ ቦሬ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ላሬ፣ ጋምቤላ እና ፉኚዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ፣ ፓዌ፣ ፉኝዶ፣ አይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሀራ፣ ቀብሪዳሃር እና ጎዴ ከ36-42 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over where the Belg rain season is the main and second rainy season, as well as in the northern and western areas of the country. Consequently, Atesbi, Aider, Debark, Metema, Gondar, Ayikel, Debretabor, Nefasmewcha, Lalibela, Wegeltena, Ambamariam, Dangila, Chagni, Debremarkos, Gundomeskel, Mankush, Bulen, Nedjo, Aira, Gimbi, Chewaka, Angergutin, Gidayana, Shambu, Nekemte, Arjo, Limugenet, Sokoru, Chira, Hosaina, Hawassa, Bilate, Bore, Tepi, Aman, Lare, Gambella and Fugnido received light to moderate rainfall. In contrast, the maximum daily temperature was recorded in Metema, Pawe, Fugnido, Aisha, Dire Dawa, Metehara, Kebridahar, and Gode, ranging from 36 to 42 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

April 8, 2025

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የጃራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ እንዲሁም ከአማራ ክልል የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደቡብና ምዕራብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ አሌ እና ደራሼ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

For the upcoming day, there will be cloud coverage in areas of the country where Belg is the main and second rainy season as well as the north west portions of our country. Along with this, from the south Ethiopian region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, south Omo and Gedeo zones; from the South west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Somali region Jarar, Erer, Nogob, Korahe, Shebelle, Afder, Liben and Dawa zones; Sidama region zones; from Oromia region Guji and west Guji, east Hararge, Bale and east Bale, Borena and east Borena, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega and west Arsi zones; from central Ethiopia region Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak and Majang zones; as well as from Amhara region west and central Gondar, Awi zone and west Gojam zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Mao Komo and Kamashi zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Besides, the south and west Omo, Gamo, Ale, and Derashe zones will experience heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours. Conversely, in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Abobo, Fugnido, and Gode will the maximum daily temperature exceeds 38 degrees Celsius.