Daily Weather Report 25 Apr 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም ሻሁራ፣ጎንደር፣ ቻግኒ፣ ጊዳአያና፣ ጊምቢ፣ አርጆ፣ ደምቢዶሎ፣ ጎሬ፣ ጂንካ፣ ምዕራብ አባያ፣ ዲላ እና ዶሎ ኦዶ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በጨዋቃ፣ ጎዴ እና አዋሽ አርባ ከ38-39 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was a cloud cover over the areas of our country that benefited from the autumn rains. In connection with this, light rain was recorded in Shahura, Gondar, Chagni, Gidayana, Gimbi, Arjo, Dembidolo, Gore, Jinka, West Abaya, Dilla and Dolo Odo. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Chewaka, Gode and Awash Arba between 38-39 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ እና ሰሜን ሸዋ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክና ማጃንግ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ባስኬቶ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀዲያ እና ከምባታ፤ የሲዳማ ክልል፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ ዳልፋጊ እና ገዋኔ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg. Along with this, the western part of Tigray region; the western, central and northern Gondar, western and eastern Gojam, Awi and northern Shewa regions of Amhara region; From the Oromia region, Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, East and West Hararge, Horogudru, Kelem, West and East Wellega, Guji and West Guji, Bale, West Arsi, West, East and South-West Shewa; Dire Dawa, Harar; from the Benishangul Gumuz region, Metekel, Asosa and Mao Komo; Itang, Agnuak and Majang zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones of Southwestern Ethiopia region; Wolaita, Gamo, Gofa and Basketo zones of Southern Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya and Kembata zones of Central Ethiopia region; Sidama region, Fafen, Dawa, Liben and Afder zones of Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, our forecast data indicates that Ilubabor, Sheka, Kefa and Dawuro zones will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the maximum daily temperature will be recorded above 38-40 degrees Celsius in Humera, Metekele, Gambella, Abobo, Fugendo, Lare, Dalifagi and Gewane.