Daily Weather Report 25 Apr 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በአይከል፣ ቻግኒ፣ መተከል፣ ነጆ፣ ፉኝዶ፣ ዲላ፣ አደሌ፣ ጃራ፣ ሐረር፣ ኮንሶ፣ ቦሬ እና ሽላቦ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በአዋሽ አርባ፣ ዱብቲ ፣ ጎዴ እና ገዋኔ ከ38-43.8 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the belg main and second rainy seasons of our country. In connection with this, light rain was recorded in Aikel, Chagni, Metekel, Nejo, Fugendo, Dilla, Adele, Jara, Harar, Konso, Bore and Shlabo. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Awash Arba, Dubti, Gode and Gewane between 38-43.8 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክና ማጃንግ ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ባስኬቶ ፣ የሲዳማ ክልል፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ሸበሌ፣ ዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ፓዌ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አዋሽ አርባ፣ ዳልፋጊ እና ገዋኔ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow Our forecast data indicates that there will be better cloud cover in the areas of our country that benefit from the belg rains. In connection with this, the western part of Tigray region; the western, central and northern Gondar, western and eastern Gojam and Awi regions of Amhara region; From the Oromia region, Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, East and West Hararge, Horogudru, Kelem, West and East Wellega, Guji and West Guji, Bale; Dire Dawa, Harar; from the Benishangul Gumuz region, Metekel, Asosa and Mao Komo; from the Gambella region, Itang, Anuak and Majang; from the Southwestern Ethiopia region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; The Wolaita, Gamo, Gofa and Basketo zones of the Southern Ethiopian Region, Sidama Region, and the Fafen, Jarar, Shebele, Dawa, Liben and Afder zones of the Somali Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, the maximum daily temperature will be recorded above 38-40 degrees Celsius in Humera, Metema, Qara, Pawe, Metekel, Gambella, Abobo, Fugendo, Lare, Awash Arba, Dalfagi and Gewane.